1 ነገሥት 15:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ጌታ ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር ጌታን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ዳዊት በኬጢያዊው በኦርዮ ላይ ካደረሰው በደል በቀር፣ በእግዚአብሔር ፊት ትክክል የሆነውን ነገር አድርጓል፤ በሕይወት ዘመኑም ሁሉ ከእግዚአብሔር ትእዛዝ ፈቀቅ ያለበት ጊዜ አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 እግዚአብሔር ይህን ያደረገበት ምክንያት ዳዊት በሒታዊው ኦርዮን ላይ ከፈጸመው ኃጢአት በቀር እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር በማድረጉና ትእዛዙንም በብርቱ ጥንቃቄ በመጠበቁ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ከኬጥያዊው ከኦርዮ ነገር በቀር ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገርን አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ዳዊት በዘመኑ ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ቅን ነገር አድርጎ ነበርና፥ ካዘዘውም ነገር ሁሉ ፈቀቅ አላለም ነበርና። ምዕራፉን ተመልከት |