1 ነገሥት 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ይሁን እንጂ የኢዮርብዓም ሚስት ስለታመመው ልጇ ልትጠይቀው እንደምትመጣና ምን ሊነግራት እንደሚገባውም ጌታ አስቀድሞ ለነቢዩ አኪያ ገልጦለት ነበር። የኢዮርብዓም ሚስት እዚያ በደረሰች ጊዜ ሌላ ሴት ለመምሰል ሞከረች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 እግዚአብሔር ግን ለአኪያ፣ “እነሆ፤ የኢዮርብዓም ሚስት ስለ ታመመው ልጇ ልትጠይቅህ ሌላ ሴት መስላ ትመጣለችና እንዲህ ብለህ መልሳት” ብሎ ነገረው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ይሁን እንጂ የኢዮርብዓም ሚስት ስለታመመው ልጅዋ ልትጠይቀው እንደምትመጣና ምን ሊነግራት እንደሚገባውም እግዚአብሔር አስቀድሞ ለነቢዩ አኪያ ገልጦለት ነበር። የኢዮርብዓም ሚስት እዚያ በደረሰች ጊዜ ሌላ ሴት ለመምሰል ሞከረች፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እግዚአብሔርም አኪያን፥ “እነሆ፥ ስለ ታመመው ልጅዋ ትጠይቅህ ዘንድ የኢዮርብዓም ሚስት ትመጣለች፤ ራስዋንም ለውጣ ወደ አንተ በገባች ጊዜ እንዲህና እንዲህ በላት” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 እግዚአብሔርም አኪያን “እነሆ፥ ስለ ታመመው ልጅዋ ትጠይቅህ ዘንድ የኢዮርብዓም ሚስት ትመጣለች፤ ሌላ ሴትም መስላ ተሰውራለችና በገባች ጊዜ እንዲህና እንዲህ በላት፤” አለው። ምዕራፉን ተመልከት |