1 ነገሥት 14:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 በዚህ ምክንያት እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነጻም ሆነ ባርያ፥ ወንድ ልጅንም ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 “ ‘ስለዚህ እኔም በኢዮርብዓም ቤት ላይ ጥፋትን አመጣለሁ፤ ባሪያም ይሁን ነጻ ዜጋ የኢዮርብዓምን ወንድ ልጅ ሁሉ ከእስራኤል አስወግዳለሁ፤ ኩበትም ዐመድ እስኪሆን ድረስ እንደሚቃጠል፣ እኔም የኢዮርብዓምን ቤት እንዲሁ አቃጥላለሁ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 በዚህ ምክንያት እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ ክፉ ነገርን አመጣለሁ፤ ከቤቱም ነጻም ሆነ ባሪያ፥ ወንድ ልጅን ሁሉ ከእስራኤል አጠፋለሁ፤ ፋንድያን አቃጥለው እንደሚጨርሱት የኢዮርብዓምን ቤት አወድማለሁ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ስለዚህ እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ መከራን አመጣለሁ፤ ኢዮርብዓምንም አጠፋዋለሁ፤ አጥር ተጠግቶ እስከሚሸን ወንድ ድረስ አላስቀርለትም፤ በእስራኤልም ላይ ይነግሥ ዘንድ አልተወውም፤ ሰው ገለባ እስኪያልቅ ድረስ እንደሚያነድድ በኢዮርብዓም ቤት ላይ እሳትን አነዳለሁ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ስለዚህ፥ እነሆ፥ በኢዮርብዓም ቤት ላይ መከራ አመጣለሁ፤ ከኢዮርብአምም በእስራኤል ዘንድ የታሰረውንና የተለቀቀውን ወንድ ሁሉ እቆርጣለሁ፤ ሰውም ፋንድያን እስኪጠፋ ድረስ እንደሚጠርግ እኔ የኢዮርብዓምን ቤት ፈጽሜ እጠርጋለሁ። ምዕራፉን ተመልከት |