1 ነገሥት 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 ንጉሡም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም4 ንጉሥ ኢዮርብዓምም ያ የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል መሠዊያ ላይ ጮኾ የተናገረውን ሲሰማ፣ እጁን መሠዊያው ካለበት በመዘርጋት፣ “ያዙት!” አለ፤ ነገር ግን ያች የዘረጋት እጁ ደርቃ ቀረች፤ ሊመልሳትም አልቻለም ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 ንጉሥ ኢዮርብዓምም ይህን በሰማ ጊዜ እጁን አንሥቶ ወደ ነቢዩ በማመልከት! “ያዙት!” የሚል ትእዛዝ ሰጠ፤ የንጉሡም ክንድ ወዲያውኑ ድርቅ ብሎ ሽባ ስለ ሆነ የዘረጋውን እጁን መመለስ አልቻለም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኢዮርብዓም የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ የተናገረውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ንጉሡ፥ “ያዙት” ብሎ እጁን ከመሠዊያው ላይ አነሣ። ከዚህም በኋላ በእርሱ ላይ የዘረጋት እጁ ደረቀች፤ ወደ እርሱም ይመልሳት ዘንድ አልተቻለውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 ንጉሡም የእግዚአብሔር ሰው በቤቴል ባለው መሠዊያ ላይ የጮኸውን ነገር በሰማ ጊዜ፥ ኢዮርብዓም እጁን ከመሠዊያው አንሥቶ “ያዙት!” አለ። በእርሱም ላይ የዘረጋት እጅ ደረቀች፤ ወደ እርሱም ይመልሳት ዘንድ አልተቻለውም። ምዕራፉን ተመልከት |