Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 11:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 በደል በመሥራትም ጌታን አሳዘነ፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በቅንነት በመከተል ረገድ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ስለዚህ ሰሎሞን በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ድርጊት ፈጸመ፤ እንደ አባቱ እንደ ዳዊትም እግዚአብሔርን እስከ መጨረሻው አልተከተለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 በደል በመሥራትም እግዚአብሔርን አሳዘነ፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በቅንነት በመከተል ረገድ እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ነገ​ርን አደ​ረገ፤ እንደ አባ​ቱም እንደ ዳዊት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አል​ተ​ከ​ተ​ለ​ውም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ሰሎሞንም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገርን አደረገ፤ እንደ አባቱም እንደ ዳዊት እግዚአብሔርን በመከተል ፍጹም አልሆነም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 11:6
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይህንንም የማደርገው ሰሎሞን እኔን ትቶ ባዕዳን የሆኑትን ዐስታሮት ተብላ የምትጠራውን የሲዶና አምላክ፥ ኬሞሽ ተብሎ የሚጠራውን የሞዓብ አምላክና ሚልኮም ተብሎ የሚጠራውን የዐሞን አምላክ ስላመለከ ነው፤ ሰሎሞን ለእኔ ታዛዥ አልሆነም፤ እርሱ አባቱ ዳዊት ለእኔ ይታዘዝ እንደ ነበር ሕጎቼንና ትእዛዞቼን ባለመጠበቁ በድሎአል።


የሲዶናውያን ሴት አምላክ ለነበረችው ለዐስታሮትና ሞሎክ ተብሎ ለሚጠራው ለአጸያፊው ለዐሞናውያን አምላክ ሰገደ።


ከኢየሩሳሌም በስተ ምሥራቅ በሚገኘው ተራራ ላይ አጸያፊዎች ለሆኑት ኬሞሽ ተብሎ ለሚጠራው ለሞአባውያን አምላክና ሞሌክ ተብሎ ለሚጠራው ለዐሞናውያን አምላክ የመስገጃ ስፍራዎችን አዘጋጀላቸው።


ሰሎሞን ጌታን ይወድ ነበር፤ የአባቱንም የዳዊትን መመሪያ ይጠብቅ ነበር፤ ይሁን እንጂ እንስሶችን እያረደ በተለያዩ ኰረብቶች ላይ መሥዋዕት ያቀርብ፥ ዕጣንም ያጥን ነበር።


አንተ ግን አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በቅንነትና በታማኝነት እኔን ብታገለግል፥ የእኔን ሕግና ሥርዓት ብትጠብቅ፥ ያዘዝኩህንም ሁሉ ብትፈጽም፥


ባርያዬ ካሌብ ግን ሌላ መንፈስ ከእርሱ ጋር ስለ ሆነ ፈጽሞም ስለ ተከተለኝ እርሱ ሄዶ ወደ ነበረበት ምድር አገባዋለሁ፤ ዘሩም ይወርሳታል።


ስለዚህም የእስራኤል አምላክ ጌታን ፈጽሞ ስለ ተከተለ ኬብሮን እስከ ዛሬ ለቄኔዛዊው ለዮፎኒ ልጅ ለካሌብ ርስት ሆነች።


ከእኔ ጋር የወጡ ወንድሞቼ ግን የሕዝቡን ልብ በፍርሃት አቀለጡ፤ እኔ ግን አምላኬን ጌታን ፈጽሜ ተከተልሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች