Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 10:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

26 ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉ ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፥ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

26 ሰሎሞን ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺሕ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺሕ ፈረሶች ነበሩት፤ እነርሱንም በሠረገላ ከተሞችና ንጉሡ ባለበት በኢየሩሳሌም ከተማ አኖራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

26 ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሶችን ሰበሰበ፤ እርሱም አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎችና ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሰኞች ነበሩት፤ ከእነርሱም ከፊሉ ከእርሱ ጋር በኢየሩሳሌም፥ ሌሎቹ ደግሞ በልዩ ልዩ ከተሞች ተመድበው እንዲኖሩ አደረገ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

26 ሰሎ​ሞ​ንም ለሰ​ረ​ገ​ሎቹ ዐራት ሺህ እን​ስት ፈረ​ሶች ነበ​ሩት፤ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረ​ሰ​ኞ​ችም ነበ​ሩት፤ በሰ​ረ​ገ​ሎ​ችም ከተ​ሞች ከን​ጉሡ ጋር በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አኖ​ራ​ቸው። ሰሎ​ሞ​ንም ከወ​ንዙ ጀምሮ እስከ ፍል​ስ​ጥ​ኤም ምድ​ርና እስከ ግብፅ ድን​በር ድረስ በነ​ገ​ሥ​ታቱ ሁሉ ላይ ንጉሥ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

26 ሰሎሞንም ሠረገሎችንና ፈረሰኞችን ሰበሰበ፤ አንድ ሺህ አራት መቶ ሠረገሎች፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፤ በሠረገሎችም ከተሞች ከንጉሡም ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 10:26
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሎሞንም ለፈረሶችና ለሰረገሎች አራት ሺህ ጋጥ፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፥ በሰረገሎችም ከተሞች፥ ከንጉሡም ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።


ሰሎሞን ሠረገላ የሚስቡ አርባ ሺህ ቅልብ ፈረሶችና ለጦርነት የሚያገለግሉ ዐሥራ ሁለት ሺህ ፈረሶች ነበሩት።


እነዚህም የስንቅ ማከማቻዎች፥ ፈረሶችና ሠረገሎች የሚጠበቁባቸው፥ ከተሞችን ከተመ፤ ሰሎሞንም በኢየሩሳሌም፥ በሊባኖስና በግዛቱ ሁሉ የሚፈልገውን ገነባ።


ንጉሡም ብዙ ፈረሶችን ለራሱ አያብዛ፤ ወይም ደግሞ ፈረሰኞች ለማብዛት ሕዝቡን ወደ ግብጽ አይመልስ፤ ጌታ፥ ‘በዚያ መንገድ ፈጽሞ አትመለሱ’ ብሎአችኋልና።


ምድራቸው በብርና በወርቅ ተሞልታለች፤ ሀብታቸውም ልክ የለውም። ምድራቸው በፈረሶች ተሞልታለች፤ የሠረገሎቻቸውም ብዛት ልክ የለውም።


ስለዚህ የሊባኖስ ዛፍ እንጨት የሚቆርጡ ሰዎችን ወደ ሊባኖስ ላክልኝ፤ የእኔም ሰዎች ከእነርሱ ጋር አብረው እንዲሠሩ አደርጋለሁ፤ ለሰዎችህም አንተ የምትወስነውን ደመወዝ እከፍላለሁ፤ አንተ እንደምታውቀው የእኔ ሰዎች ስለ ዛፍ አቆራረጥ የአንተን ሰዎች ያኽል ዕውቀት የላቸውም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች