1 ነገሥት 10:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)22 ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም22 ንጉሡ ከኪራም መርከቦች ጋራ ዐብረው በባሕር ላይ የሚጓዙ የተርሴስ የንግድ መርከቦች ነበሩት። እነዚህም በየሦስት ዓመቱ አንድ ጊዜ ወርቅ፣ ብርና የዝሆን ጥርስ፣ ጦጣዎችና ዝንጀሮዎች ያመጡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም22 ሰሎሞን ከኪራም መርከቦች ጋር በውቅያኖስ ላይ የሚጓዙ ሌሎች የተርሴስ መርከቦችም ነበሩት፤ እነርሱም በየሦስት ዓመት ወርቅን፥ ብርን፥ የዝሆን ጥርስን፥ ጦጣዎችንና ዝንጀሮዎችን ያመጡለት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)22 ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር በባሕር ውስጥ የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በየሦስት ዓመትም አንድ መርከብ ከተርሴስ ወርቅና ብር፥ የተቀረጸና የተደረደረ ዕንቍ ይዞ ይመጣ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)22 ለንጉሡም ከኪራም መርከቦች ጋር የተርሴስ መርከቦች ነበሩት፤ በሦስት በሦስት ዓመትም አንድ ጊዜ የተርሴስ መርከቦች ወርቅና ብር፥ የዝሆንም ጥርስ፥ ዝንጀሮና ዝንጕርጕር ወፍ ይዘው ይመጡ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |