1 ነገሥት 10:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ንጉሥ ሰሎሞን ከተለመደው የልግስና ስጦታው ጋር የሳባ ንግሥት የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ከዚህ በኋላ ንግሥተ ሳባ ከክብር አጃቢዎችዋ ጋር ወደ አገርዋ ተመልሳ ሄደች። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 ንጉሥ ሰሎሞንም ለሳባ ንግሥት ከቤተ መንግሥቱ በልግስና ከሚሰጣት ሌላ፣ የፈለገችውንና የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ከዚያም ከአጃቢዎቿ ጋራ ወደ አገሯ ተመለሰች። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 ንጉሥ ሰሎሞን ከተለመደው የልግሥና ስጦታው ጋር የሳባ ንግሥት የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣት፤ ከዚህ በኋላ ንግሥተ ሳባ ከክብር አጃቢዎችዋ ጋር ወደ አገርዋ ተመልሳ ሄደች። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 ንጉሡም ሰሎሞን በእጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን ሁሉ፥ ከእርሱም የጠየቀችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት፤ የከለከላትም የለም፤ እርስዋም ተመልሳ ከአገልጋዮችዋ ጋር ወደ ሀገርዋ ሄደች። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 ንጉሡም ሰሎሞን፥ በገዛ እጁ ከሰጣት ሌላ፥ የወደደችውን ሁሉ ከእርሱም የለመነችውን ሁሉ ለሳባ ንግሥት ሰጣት፤ እርስዋም ተመልሳ ከባሪያዎችዋ ጋር ወደ ምድርዋ ሄደች። ምዕራፉን ተመልከት |