Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 1:45 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

45 ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፥ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፥ ከተማይቱም አስተጋባች፥ የሰማችሁትም ድምፅ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

45 ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ቀብተው አንግሠውታል። ከዚያም ደስ ብሏቸው ወጥተዋል፤ ከተማዪቱም ይህንኑ አስተጋብታለች፤ እንግዲህ የሰማችሁት ድምፅ ይኸው ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

45 ካህኑ ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ምንጭ አጠገብ ቀብተው አንግሠውታል፤ ከዚህም በኋላ ሕዝቡ ሁሉ በደስታ ተሞልተው በእልልታና በሆታ ድምፃቸው እያስተጋባ ወደ ከተማ ተመልሰዋል፤ አሁን የምትሰሙትም ድምፅ ይኸው ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

45 ካህ​ኑም ሳዶ​ቅና ነቢዩ ናታን ቀብ​ተው በግ​ዮን አነ​ገ​ሡት፤ ከዚ​ያም ደስ ብሎ​አ​ቸው ወጡ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱም አስ​ተ​ጋ​ባች፤ የሰ​ማ​ች​ሁ​ትም ድምፅ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

45 ካህኑም ሳዶቅና ነቢዩ ናታን በግዮን ንጉሥ አድርገው ቀቡት፤ ከዚያም ደስ ብሎአቸው ወጡ፤ ከተማይቱም አስተጋባች፤ የሰማችሁትም ድምጽ ይህ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 1:45
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝቡም ሁሉ እርሱን ተከትለው ወጡ፥ ሕዝቡም ዘፈን ይዘፍኑ ነበር፥ በታላቅም ደስታ ደስ አላቸው፥ ከጩኸታቸውም የተነሣ ምድር ተናወጠች።


ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፥ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።


ነገር ግን ነቢዩ አኪያ ወደ በሩ ስትቀርብ የኮቴዋን ድምፅ ሰምቶ እንዲህ አላት፥ “ግቢ! የኢዮርብዓም ሚስት መሆንሽን ዐውቃለሁ፤ ሌላ ሴት ለመምሰል ስለምን ሞከርሽ? ለአንቺ እነግርሽ ዘንድ የታዘዝኩት አሳዛኝ ዜና አለ።


ሕዝቡ ግን ደስ ብሎአቸው የሚጮኹትን ድምፅ ከሕዝቡ ልቅሶ ድምፅ መለየት አልቻለም፤ ሕዝቡም በታላቅ ድምፅ እልል ይሉ ነበር፥ ድምፁም ከሩቅ ይሰማ ነበር።


እርሱም፥ “መልኩ ምን ይመስላል?” ሲል ጠየቃት። እርሷም፥ “ካባ የለበሰ አንድ ሽማግሌ ሰው እየወጣ ነው” አለችው። ሳኦልም ሴትዮዋ ያየችው ሳሙኤል መሆኑን ዐወቀ፤ በመሬትም ላይ ተደፍቶ እጅ ነሣ።


የጌታ የኪዳኑ ታቦት ወደ ሰፈር በገባ ጊዜ፥ ምድር እስክትናወጥ ድረስ እስራኤላውያን ሁሉ ታላቅ የሆታ ድምፅ አሰሙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች