Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 በሁሉም የእስራኤል ግዛት የተዋበች ቆንጆ ፈለጉ፤ አቢሻግንም ሹኔም ከምትባል ስፍራ አገኙ፤ ወደ ንጉሡም ይዘዋት መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ከዚያም በመላው እስራኤል ቈንጆ ልጃገረድ ፈልገው ሱነማዪቱን አቢሳን አገኙ፤ ለንጉሡም አመጡለት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 አንዲት ቈንጆ ልጃገረድ ለማግኘት በመላው እስራኤል ፍለጋ ተደረገ፤ ሹኔም ተብላ ከምትጠራው ስፍራ አቢሻግ የምትባል አንዲት ልጃገረድ አግኝተው ለንጉሡ አመጡለት፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሀገር ሁሉ የተ​ዋ​በች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነ​ማ​ዪ​ቱን አቢ​ሳ​ንም አገኙ፤ ወደ ንጉ​ሡም ወሰ​ዱ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 በእስራኤልም አገር ሁሉ የተዋበች ቆንጆ ፈለጉ፤ ሱነማይቱን አቢሳንም አገኙ፤ ወደ ንጉሡም ይዘዋት መጡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 1:3
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ድንበራቸውም የሚያጠቃልለው ኢይዝራኤልን፥ ከስሎትን፥ ሱነምን፥


አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤


ፍልስጥኤማውያን ተሰብስበው በመምጣት በሹኔም ሲሰፍሩ፥ ሳኦል ደግሞ እስራኤላውያንን ሁሉ ሰብስቦ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ሰፈረ።


እርሷም ከዚያ ተነሥታ ኤልሳዕ ወደ ነበረበት ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ወጣች። ኤልሳዕም ገና በሩቅ ሳለች ወደ እርሱ ስትመጣ አይቶ አገልጋዩን ግያዝን “ተመልከት! ያቺ ሴት ከሱነም ወደዚህ በመምጣት ላይ ናት!


ባርያዎቹም፦ “ንጉስ ሆይ! ከአንተ ጋር ሆና የምትንከባከብህ ወጣት ልጃገረድ ፈልገን እናምጣ፤ በጌታችንም በንጉሡ እቅፍ ተኝታ ታሞቅሃለች” አሉት።


ልጃገረዲቱም እጅግ ውብ ነበረች። ለንጉሡም ረዳትና አገልጋይ ሆነች፤ ንጉሡ ግን ከእርሷ ጋር ግንኙነት ፈጽሞ አያውቅም ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች