Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ነገሥት 1:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ እጅ ነሣች፥ ንጉሡም፦ “ምን ትፈልጊያለሽ?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ቤርሳቤህም ለጥ ብላ እጅ ከነሣች በኋላ እፊቱ በጕልበቷ ተንበረከከች። ንጉሡም፣ “ምን ትፈልጊያለሽ?” ሲል ጠየቃት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ቤርሳቤህም ወደ መሬት ለጥ ብላ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ቤር​ሳ​ቤ​ህም አጎ​ን​ብሳ ለን​ጉሡ ሰገ​ደች፤ ንጉ​ሡም፥ “ምን ሆንሽ?” አላት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ቤርሳቤህም አጎንብሳ ለንጉሡ እጅ ነሣች፤ ንጉሡም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ነገሥት 1:16
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቤርሳቤህም ወደ ንጉሡ እልፍኝ ገባች፥ ንጉሡም እጅግ ሸምግሎ ነበር፥ ሹኔማይቱም አቢሻግ ታገለግለው ነበር።


እርሷም አለችው፦ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ለባርያህ፦ ‘ልጅሽ ሰሎሞን ከእኔ በኋላ ይነግሣል፥ በዙፋኔም ይቀመጣል’ ብለህ በጌታ በእግዚአብሔር ምለህልኛል፥


ለንጉሡም፦ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቷል” ብለው ነገሩት፥ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግምባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ።


እርሷም “እንድትፈጽምልኝ የምጠይቅህ አንድ ትንሽ ጉዳይ አለኝ፤ እባክህ እምቢ በማለት አታሳፍረኝ” አለችው። ንጉሡም “እናቴ ሆይ! አላሳፍርሽም፤ ጉዳዩ ምንድነው” አላት።


እርሱም “ምን ትፈልጊያለሽ?” አላት። እርሷም “እነዚህ ሁለቱ ልጆቼ በመንግሥትህ አንዱ በቀኝህ አንዱ በግራህ እንዲቀመጡ እዘዝ” አለችው።


ኢየሱስም ቆሞ ጠራቸውና “ምን እንዳደርግላችሁ ትፈልጋላችሁ?” አላቸው።


ልጁ ከሄደ በኋላ፥ ዳዊት ከድንጋዩ በስተ ደቡብ ከተደበቀበት ቦታ ወጥቶ በዮናታን ፊት ሦስት ጊዜ በምድር ላይ ተደፍቶ ሰገደለት፤ ከዚያም ተሳሳሙ፤ ተላቀሱም፤ በይበልጥ ያለቀሰው ግን ዳዊት ነበር።


ዳዊት ሰዎቹን በዚህ ቃል ከለከላቸው፤ በሳኦል ላይ አደጋ እንዲያደርሱበትም አልፈቀደላቸውም። ሳኦልም ከዋሻው ወጥቶ ሄደ።


አቢግያም ዳዊትን ባየች ጊዜ ወዲያው ከአህያዋ ወርዳ፥ በዳዊትም ፊት በግምባርዋ ተደፍታ እጅ ነሣች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች