Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዮሐንስ 3:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ልባችን ቢወቅሰን እንኳ እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉንም ያውቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ይህም ልባችን በእኛ ላይ በሚፈርድብን ነገር ሁሉ ነው። እግዚአብሔር ከልባችን ይልቅ ታላቅ ነውና ሁሉን ነገር ያውቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 በዚህ በኩል ልባችን ቢወቅሰንም እግዚአብሔር ከልባችን በላይ ነው፤ እርሱም ሁሉን ነገር ያውቃል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዮሐንስ 3:20
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“እኔ ጌታ ለሰው ሁሉ እንደ መንገዱ፥ እንደ ሥራው ፍሬ ለመስጠት ልብን እመረምራለሁ ኩላሊትንም እፈትናለሁ።”


በፊቱም የሚሰወር ምንም ፍጥረት የለም፤ እኛ መልስ መስጠት በሚገባን ከእርሱ ፊት ሁሉ ነገር ግልጥና ዕርቃኑን ሆኖ የሚታይ ነው።


በራሴ ላይ ከኅሊናዬ ምንም የለም፤ ነገር ግን በዚህ አልጸድቅም፤ በእኔ ላይ የሚፈርድ ግን ጌታ ነው።


ልጆች ሆይ፥ እናንተ ከእግዚአብሔር ናችሁ፥ አሸንፋችኋቸዋልም፥ በእናንተ ያለው በዓለም ካለው ይበልጣልና።


ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ።


እነሆ፥ አንተ በዚህ አቋምህ ትክክል አይደለህም፥ ‘እግዚአብሔር ከሰው ይበልጣል’ ብዬ እመልስልሃለሁ።


ለሦስተኛ ጊዜም “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! ትወደኛለህን?” አለው። ለሦስተኛ ጊዜ “ትወደኛለህን?” ስላለው ጴጥሮስ አዘነና “ጌታ ሆይ! አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው። ኢየሱስም “በጎቼን አሰማራ።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


የተሰወረውን መተላለፋችንን በፊትህ ብርሃን፥ ምሥጢራችንን በፊትህ አስቀመጥህ።


እንዲህ ዓይነቱ ሰው ጠማማና ኃጢአተኛ በመሆኑ በራሱ ላይ እንደፈረደ አውቀሃልና።


በጽድቄ እጸናለሁ እርሱንም አልተውም፥ ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱም እንኳን ኅሊናዬ አይወቅሰኝም።”


እነርሱም ይህን ሲሰሙ ከሽማግሌዎች ጀምሮ አንድ አንድ እያሉ ወጡ፤ ኢየሱስም ብቻውን ቀረ፤ ሴቲቱም በመካከል ቆማ ነበረች።


እግዚአብሔር ለአብርሃም ተስፋ በሰጠው ጊዜ፥ የሚምልበት ከእርሱ የበለጠ ሌላ ማንም ስለ ሌለ በራሱ ማለ፤


እነርሱም ሲሰሙ በጣም ተቆጡ፤ ሊገድሉአቸውም አሰቡ።


የሚኰንን ማን ነው? የሞተው፥ ይልቁንም ከሙታን የተነሣው፥ በእግዚአብሔር ቀኝ ያለው፥ ስለ እኛም በእርግጥ የሚያማልደው ክርስቶስ ኢየሱስ ነው።


በዚህም ከእውነት መሆናችንን እናውቃለን፥ በፊቱም ልባችንን እናሳርፋለን፥


ወዳጆች ሆይ፥ ልባችን የማይወቅሰን ከሆነ በእግዚአብሔር ዘንድ ድፍረት አለን፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች