Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ዮሐንስ 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ከመጀመሪያ የሰማችሁት መልእክት ይህ ነውና፥ እርሱም፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ከመጀመሪያ የሰማችኋት፣ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል የምትለዋ መልእክት ይህች ናትና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከመጀመሪያው የሰማችሁት መልእክት “እርስ በርሳችን እንፋቀር” የሚል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዮሐንስ 3:11
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከማእድ ተነሣ፤ ልብሱንም አኖረ፤ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤


“ትእዛዜ ይህች ናት፤ እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ።


የእርስ በርሳችሁን ሸክም ተሸከሙ፥ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።


ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።


እናንተ ራሳችሁ የእርስ በእርስ መዋደድን በእግዚአብሔር ተምራችኋልና፥ ስለ ወንድማማች መዋደድ ማንም ሊጽፍላችሁ አያስፈልጋችሁም፤


የትእዛዙ ዓላማ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ኅሊና፤ ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚመነጭ ፍቅር ነው፤


ለእውነት በመታዘዝ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ ለወንድማማች እውነተኛ ፍቅር፥ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ እርስ በእርሳችሁ ተሳሰቡ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።


ፍቅር የኃጢአትን ብዛት ይሸፍናልና ከሁሉ በፊት እርስ በርሳችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ።


ከእርሱ የሰማነውና ለእናንተም የምንነግራችሁ መልእክት ይህ ነው፦ እግዚአብሔር ብርሃን ነው ጨለማም በእርሱ ዘንድ ከቶ የለም።


ወዳጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር እንዲህ ከወደደን፥ እኛ ደግሞ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል።


ከእርሱ የተሰጠን ትእዛዝ ይህ ነው፥ እግዚአብሔርን የሚወድ ወንድሙን ደግሞ ይውደድ።


ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚያፈቅር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፥ እግዚአብሔርንም ያውቃል።


አሁንም እመቤት ሆይ! አዲስን ትእዛዝ አልጽፍልሽም ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረውን ነው፥ ይህም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች