Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 8:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ምንም እንኳ፥ በሰማይ ሆነ በምድርም፥ አማልክት ተብለው የሚጠሩ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 መቼም ብዙ “አማልክትና” ብዙ “ጌቶች” አሉ፤ በሰማይም ሆነ በምድር አምላክ ተብለው የሚጠሩ አማልክት ቢኖሩም፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ምንም እንኳ አምላክ ሳይሆኑ አማልክት ተብለው የሚጠሩ ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች በሰማይም ሆነ በምድር አሉ ቢባል

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 አማ​ል​ክት የሚ​ሉ​አ​ቸው ነገ​ሮች አሉና፤ በሰ​ማ​ይም ቢሆን፥ በም​ድ​ርም ቢሆን፥ ብዙ አማ​ል​ክ​ትና ብዙ ጌቶች ቢኖሩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 8:5
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለአሳፋሪ ነገር መሠዊያዎችን ሠርታችኋል፥ እነርሱም ለበዓል የምታጥኑባቸው መሠዊያዎች ናቸው።


በውኑ አማልክት ያልሆኑትን አማልክቱን የለወጣቸው አንድ ሕዝብ አለን? ነገር ግን ሕዝቤ ክብሩን በማይረባ ነገር ለወጠ።


ለራስህ የሠራሃቸው አማልክትህ ወዴት ናቸው? ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር ብዛት እንዲሁ ናቸውና እስቲ ይነሡ በመከራህም ጊዜ ያድኑህ።


ስለዚህ ተሰብስበው ሳሉ ጲላጦስ “ማንን ልፍታላችሁ ኢየሱስ በርባንን ወይስ ክርስቶስ የተባለውን ኢየሱስን?” አላቸው።


ነገር ግን ቀድሞ እግዚአብሔርን ሳታውቁ፥ በተፈጥሮአቸው አማልክት ላልሆኑት ተገዝታችሁ ነበር፤


ምክንያቱም ጌታ እግዚአብሔር የአማልክት አምላክ፥ የጌቶችም ጌታ፥ ታላቅ አምላክ፥ ኃያልም፥ የሚያስፈራም፥ በፍርድ የማያደላ፥ ጉቦም የማይቀበል ነው።


እርሱም ሰው የሚያመልከውን ነገር ወይም አማልክት ነን ከሚሉት ሁሉ በላይ ራሱን ከፍ ከፍ በማድረግና በመቃወም፦ “እኔ እግዚአብሔር ነኝ” ብሎ ያውጃል፤ በእግዚአብሔርም ቤተ መቅደስ ይቀመጣል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች