Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 7:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

29 ዳሩ ግን ወንድሞች ሆይ! ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

29 ወንድሞች ሆይ፤ ሐሳቤ እንዲህ ነው፤ ዘመኑ ዐጭር ነው፤ ከእንግዲህ ሚስት ያላቸው እንደሌላቸው ሆነው ይኑሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

29 ወንድሞች ሆይ! እኔ የምላችሁ እንዲህ ነው፤ ዘመኑ አጥሮአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስት ያለችው ሚስት እንደሌለችው ሆኖ ይኑሩ። ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌሉአቸው ሆነው ይኑር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

29 ነገር ግን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን እን​ዲህ ይቀ​ናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያ​ልፍ ቀር​ቦ​አ​ልና፤ አሁ​ንም ያገቡ እን​ዳ​ላ​ገቡ ይሆ​ናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

29 ዳሩ ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 7:29
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዓለምና ምኞቱ ያልፋሉ፤ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የሚያደርግ ግን ለዘለዓለም ይኖራል።


በዚችም ዓለም የሚጠቀሙ በሙሉ እንደማይጠቀሙባት ይሁኑ፤ የዚች ዓለም መልክ አላፊ ነውና።


የሁሉ ነገር መጨረሻ ተቃርቧል፤ እንግዲህ መጸለይ እንድትችሉ የረጋ አእምሮ ይኑራችሁ፤ በመጠንም ኑሩ።


ምክንያቱም፥ “ሥጋ ሁሉ እንደ ሣር፥ ክብሩም ሁሉ እንደ ሜዳ አበባ ነውና፤ ሣሩ ይጠወልጋል አበባውም ይረግፋል፤


አንተ በምትሄድበት በሲኦል ሥራና አሳብ እውቀትና ጥበብ አይገኙምና እጅህ ለማድረግ የምታገኘውን ሁሉ እንደ ኃይልህ አድርግ።


ሰው በከንቱ የሕይወቱ ቀናት ቍጥር ና እንደ ጥላ በሚያሳልፈው ዘመኑ በሕይወቱ ሳለ ለሰው የሚሻለውን የሚያውቅ ማነው? ወይስ ከፀሐይ በታች ከእርሱ በኋላ የሚሆነውን ለሰው ማን ይነግረዋል?


ጊዜው መጥቷል፥ ቀኑ ቀርቧል፥ የሚገዛ ደስ አይበለው የሚሸጥም አያልቅስ፥ ቁጣ ብዙዎች ሁሉ ላይ ነውና።


ብታገባ ግን ኃጢአት አትሠራም፤ ድንግሊቱም ብታገባ ኃጢአት አትሠራም፤ ነገር ግን እንዲህ በሚያደርጉ በሥጋቸው ላይ መከራ ይገጥማቸዋል፤ እኔም ከዚያ ባስጣልኳችሁ ነበር።


የሚያለቅሱም እንደማያለቅሱ፥ ደስ የሚላቸውም ደስ እንደማይላቸው፥ የሚገዙም ምንም እንደሌላቸው፥


ንጉሡም ባርዚላይ፥ “ከእኔ ጋር ተሻገርና በኢየሩሳሌም አብረኸኝ ኑር፤ የሚያስፈልግህን እኔ አደርግልሃለሁ” አለው።


ሌላውም ‘ሚስት አግብቼአለሁ፤ ስለዚህም ልመጣ አልችልም’ አለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች