Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 4:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንደምወዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልገሥጻችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ይህን አልጽፍም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ይህን የምጽፍላችሁ እንደ ተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ብዬ አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 እኔ ይህን የምጽፍላችሁ እንደ ተወደዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልመክራችሁ አስቤ ነው እንጂ ላሳፍራችሁ ብዬ አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 ይህ​ንም የጻ​ፍ​ሁ​ላ​ችሁ ላሳ​ፍ​ራ​ችሁ አይ​ደ​ለም፤ ልጆ​ችና ወዳ​ጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ ልመ​ክ​ራ​ች​ሁና ላስ​ተ​ም​ራ​ችሁ ነው እንጂ፤ እኔ ለሁ​ላ​ችሁ ቤዛ​ችሁ ነኝ፤ እና​ንተ ግን አላ​ፈ​ራ​ች​ሁ​ኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እንደምወዳችሁ ልጆቼ አድርጌ ልገሥጻችሁ እንጂ ላሳፍራችሁ ይህን አልጽፍም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 4:14
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባት ለልጁ እንደሚሆነው እኛም እንዴት ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሆንን እናንተው ታውቁታላችሁ፥


ልጆቼ በእውነት እንደሚመላለሱ ከመስማት የሚበልጥ ደስታ የለኝም።


እኔ ግን ከእነዚህ በአንዱም ምንም አልተጠቀምሁም። እንዲህ እንዲሆንልኝ ይህን አልጽፍም፤ ማንም ትምክህቴን ከንቱ ከሚያደርግብኝ ሞት ይሻለኛል።


በክርስቶስ አእላፍ መሪዎች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም፤ እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።


ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ሰነፎችን ገሥጹ፤ ፈሪዎችን አጽኑ፤ ደካሞችን እርዱ፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።


እኛም በክርስቶስ ፍጹም አድርገን ሁሉንም ሰው ለማቅረብ ሁሉንም ሰው እየገሠጽንና ሁሉንም ሰው በጥበብ ሁሉ እያስተማርን የምንሰብከው እርሱ ነው፤


ለእናንተ ስለ ራሳችን ሁልጊዜ መልስ የምንሰጥ ይመስላችኋልን? በእግዚአብሔር ፊት በክርስቶስ ሆነን እንናገራለን፤ ነገር ግን፥ ወዳጆቼ! እናንተን ለማነጽ ስንል ሁሉን እንናገራለን።


ስለምን? ስለማልወዳችሁ ይመስላችኋል? እንደምወዳችሁ እግዚአብሔር ያውቃል።


ይህን የምለው እናንተን ለመኮነን አይደለም፤ በአንድነት ለመሞትና በአንድነት ለመኖር በልባችን ስፍራ እንዳላችሁ አስቀድሜ ተናግሬለሁ።


ወደ ሰከነ ልቦናችሁ ተመለሱ፤ ኃጢአትንም አትሥሩ፤ እግዚአብሔርን የማያውቁ አሉና ይህንንም የምለው ላሳፍራችሁ ነው።


እንድታፍሩ ስል ይህን እላለሁ። ኧረ ለመሆኑ በወንድሞች መካከል ሽማግሌ ሊሆን የሚችል አንድ አስተዋይ ሰው አይገኝምን?


ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።


ነገር ግን ጻድቁን ኃጢአት እንዳይሠራ ብታስጠነቅቀው፥ ጻድቁም ኃጢአት ባይሠራ፥ ተጠንቅቆአልና በእርግጥ በሕይወት ይኖራል፥ አንተም ነፍስህን አድነሃል።


በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ እንደማስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነው መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።


በዚህ መልእክት በኩል ለተላከው ቃላችን የማይታዘዝ ማንም ቢኖር፥ ይህን ሰው በምልክት ለዩት፤ እንዲያፍርም ከእርሱ ጋር አትተባበሩ።


በእስራቴ ስለ ወለድሁት ስለ ልጄ ስለ ኦኔሲሞስ እለምንሃለሁ፤


ልጆቼ ሆይ፥ ይህን የምጽፍላችሁ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ብዬ ነው። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች