Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 3:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ክፍያ ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የሚተክልም ሆነ የሚያጠጣ አንድ ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን የራሱን ሽልማት ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የተከለም ሆነ ውሃ ያጠጣ እኩል ናቸው፤ እያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን ዋጋውን ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የሚ​ተ​ክ​ልም፥ የሚ​ያ​ጠ​ጣም አንድ ናቸው፤ ሁሉም እንደ ድካ​ማ​ቸው ዋጋ​ቸ​ውን ይቀ​በ​ላሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የሚተክልና የሚያጠጣ አንድ ናቸው፥ ነገር ግን እያንዳንዱ እንደ ራሱ ድካም መጠን የራሱን ደመወዝ ይቀበላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 3:8
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔር አንድ ጊዜ ተናገረ፥ እኔም ይህን ብቻ ሰማሁ፥ ኃይል የእግዚአብሔር ነው፥


በለሱን የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል፥ ጌታውንም የሚጠብቅ ይከብራል።


የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣልና፤ በዚያን ጊዜ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይከፍለዋል።


ይህናውንም ‘አንተንም በአምስት ከተማዎች ላይ ሾሜሃለው፤’ አለው።


እርሱ ለእያንዳንዱ እንደ ሥራው ይሰጠዋል፤


ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።


ማንም በዚያ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ሽልማቱን ይቀበላል፤


እንግዲህ የሚያሳድግ እግዚአብሔር እንጂ የሚተክል ሆነ ወይም የሚያጠጣ ቢሆን ምንም አይደለም።


ከእግዚአብሔር ጋር አብረን የምንሠራ ነንና፤ የእግዚአብሔር እርሻ፤ የእግዚአብሔር ሕንፃ ናችሁ።


በክርስቶስ አእላፍ መሪዎች ቢኖሩአችሁ ብዙ አባቶች የሉአችሁም፤ እኔ በክርስቶስ ኢየሱስ በወንጌል ወልጄአችኋለሁና።


ከቶ በገዛ ገንዘቡ በወታደርነት የሚያገለግል ማን ነው? ወይን ተክሎ ፍሬውን የማይበላ ማን ነው? ወይስ መንጋ እየጠበቀ ከመንጋው ወተት የማይጠጣ ማን ነው?


እያንዳንዱ የገዛ ሥራውን ይፈትን፤ ከዚያም በኋላ ስለ ራሱ ብቻ የሚመካበትን ያገኛል፥ ስለ ሌላው ግን አይደለም።


እያንዳንዱ የገዛ ራሱን ሸክም ይሸከማልና።


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማይደበዝዘውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።


የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ነገር ግን ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ።


ልጆችዋንም በሞት እገድላቸዋለሁ፤ አብያተ ክርስቲያናትም ሁሉ፥ ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ እንደሆንሁ ያውቃሉ፤ ለእያንዳንዳችሁም እንደ ሥራችሁ እሰጣችኋለሁ።


“እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች