Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 2:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ይህን ደግሞ፥ መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን፥ መንፈስ በሚያስተምረን ቃል እንናገራለን እንጂ ከሰው ጥበብ በሚገኝ ቃል አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እኛ የምንናገረው ይህን ነው፤ ከሰው ጥበብ በተማርነው ቃል ሳይሆን፣ ከመንፈስ በተማርነው ቃል እንናገራለን፤ መንፈሳዊ እውነትንም የምንገልጸው በመንፈሳዊ ቃል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ስለዚህ እኛ መንፈሳዊውን ነገር ለመንፈሳውያን ሰዎች የምናስተምረው ከሰው በሚገኘው ጥበብ ሳይሆን ከእግዚአብሔር መንፈስ በሚገኘው ጥበብ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 ይህም ትም​ህ​ር​ታ​ችን ከሰው የተ​ገኘ ትም​ህ​ርት አይ​ደ​ለም፤ የአ​ነ​ጋ​ገር ጥበ​ብም አይ​ደ​ለም፤ መን​ፈስ ቅዱስ የገ​ለ​ጸው ትም​ህ​ርት ነው እንጂ፤ መን​ፈ​ሳዊ ጥበ​ብም ከመ​ን​ፈስ ቅዱስ የሚ​ሆ​ነ​ውን መር​ም​ረው ለሚ​ያ​ውቁ ለመ​ን​ፈ​ሳ​ው​ያን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 መንፈሳዊውን ነገር ከመንፈሳዊው ነገር ጋር አስተያይተን መንፈስ በሚያስተምረን ቃል ይህን ደግሞ እንናገራለን እንጂ የሰው ጥበብ በሚያስተምረን ቃል አይደለም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 2:13
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቃሌም ስብከቴም መንፈስንና ኃይልን በመግለጥ ነበረ እንጂ፥ በሚያባብል የጥበብ ቃል አልነበረም፤


ፍጥረታዊ ሰው ግን የእግዚአብሔርን መንፈስ ነገር አይቀበለውም፤ ይህ ለእርሱ ሞኝነት ነው፥ ምክንያቱም በመንፈስ የሚመረመር ነውና፥ ሊያውቀው አይችልም።


ወንጌልን ላስተምር እንጂ ለማጥመቅ ክርስቶስ አልላከኝም፤ የክርስቶስ መስቀል ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር፥ በቃል ጥበብም አይደለም።


ወንድሞች ሆይ! እኔ ወደ እናንተ በመጣሁ ጊዜ የእግዚአብሔርን ምስጢር በቃላት መራቀቅ ወይም ጥበብ ለእናንተ ለማወጅ አልመጣሁም።


ከሰማይ በተላከ በመንፈስ ቅዱስ ወንጌልን የሰበኩላችሁ ሰዎች አሁን በነገሯችሁ ነገር፥ እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳላገለገሉ ተገለጠላቸው፥ ይህንም ነገር መላእክቱ ሊመለከቱ ይመኛሉ።


የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤


ስለ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ኃይልና መምጣቱም በነገርናችሁ ጊዜ፥ ራሳችን ግርማውን በዐይናችን አይተን የምንመሰክር እንጂ፥ በሰው ብልጠት የታቀደውን ተረት ተከትለን አይደለም።


በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ እርስ በርሳችሁ ተነጋገሩ፤ ለጌታ በልባችሁ ተቀኙና ዘምሩ፤


በልሳን የሚናገር ለእግዚአብሔር እንጂ ለሰው አይናገርምና፤ ምስጢር የሆነውን በመንፈስ ስለሚናገር የሚረዳው የለም።


እኛ መንፈሳዊን ነገር ከዘራንላችሁ፥ የእናንተን የሥጋዊን ነገር ብናጭድ ትልቅ ነገር ነውን?


መንፈስ ቅዱስ በዚያች ሰዓት ልትናገሩ የሚገባችሁን ያስተምራችኋልና።”


በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው፤ መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች