Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 16:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 አሁን ደግሞ ለቅዱሳን የሚደረገውን የገንዘብ መዋጮ በተመለከተ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት በሰጠሁት መመሪያ መሠረት አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 አሁን ደግሞ ለቅዱሳን ስለሚደረገው ገንዘብ ማሰባሰብ፤ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት በሰጠሁት ትእዛዝ መሠረት አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ለምእመናን ስለሚደረገው የገንዘብ መዋጮ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያን በሰጠሁት መመሪያ መሠረት እናንተም እንዲሁ አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ለቅ​ዱ​ሳን ስለ​ሚ​ደ​ረ​ገው አስ​ተ​ዋ​ፅኦ በገ​ላ​ትያ ላሉት ምእ​መ​ናን እንደ ደነ​ገ​ግ​ሁት እና​ን​ተም እን​ዲሁ አድ​ርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ለቅዱሳንም ገንዘብን ስለ ማዋጣት፥ ለገላትያ አብያተ ክርስቲያናት እንደ ደነገግሁት እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 16:1
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእነርሱም አጋቦስ የሚሉት አንድ ሰው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ ሊሆን እንዳለው በመንፈስ አመለከተ፤ ይህም በቀላውዴዎስ ቄሣር ዘመን ሆነ።


እንዲህም ደግሞ አደረጉ፤ በበርናባስና በሳውልም እጅ ወደ ሽማግሌዎቹ ላኩት።


በእስያም ቃሉን እንዳይናገሩ መንፈስ ቅዱስ ስለ ከለከላቸው በፍርግያና በገላትያ አገር አለፉ፤


ጥቂት ቀንም ቆይቶ ወጣ፤ ደቀ መዛሙርትንም ሁሉ እያጸና በገላትያ አገርና በፍርግያ በተራ አለፈ።


ከብዙ ዓመትም በኋላ ለሕዝቤ ምጽዋትና መሥዋዕት አደርግ ዘንድ መጣሁ፤


ሐናንያም መልሶ “ጌታ ሆይ! በኢየሩሳሌም በቅዱሳንህ ላይ ስንት ክፉ እንዳደረገ ስለዚህ ሰው ከብዙዎች ሰምቼአለሁ፤


እጁንም ለእርሷ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት።


ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ተቀበሉ።


ማንም የራበው ቢኖር፥ ለፍርድ እንዳትሰበሰቡ፥ በቤቱ ይብላ። ስለ ቀረው ነገር በመጣሁ ጊዜ መመሪያ እሰጣችኋለሁ።


ወንድሞች ሆይ፥ የእስጢፋኖስ ቤተሰቦች በአካይያ የመጀመሪያዎቹ አማኞች እንደሆኑና ቅዱሳንንም ለማገልገል ራሳቸውን እንደሰጡ ታውቃላችሁ።


በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ እንደማስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነው መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።


ከእኔም ጋር ያሉት ወንድሞች ሁሉ፥ ወደ ገላትያ አብያተ ክርስቲያናት፤


ድሆችን እንድናስብ ብቻ ለመኑን፤ እኔም ይህን ለማድረግ እተጋበት የነበረ ነው።


በጌታ በኢየሱስ ዘንድ፤ በቅዱሳንም ሁሉ ዘንድ ስላለው ፍቅርህና እምነትህ እሰማለሁና።


የቅዱሳን ልብ በአንተ ሥራ ስለ ዐረፈ፥ ወንድሜ ሆይ! በፍቅርህ ብዙ ደስታንና መጽናናትን አግኝቼአለሁና።


እግዚአብሔር፥ ቅዱሳንን ስላገለገላችሁ እስከ አሁንም ስለምታገለግሉአቸው፥ ያደረጋችሁትን ሥራ ለስሙም ያሳያችሁትን ፍቅር ይረሳ ዘንድ ዐመፀኛ አይደለምና።


ነገር ግን ማንም የዚህ ዓለም ሀብት ቢኖረው፥ ወንድሙም ተቸግሮ አይቶ ባይራራለት፥ የእግዚአብሔር ፍቅር በእርሱ እንዴት ይኖራል?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች