Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 15:52 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

52 የመጨረሻው መለከት ሲነፋ፥ ድንገት፥ በቅጽበተ ዐይን፥ መለከት ይነፋል፤ ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

52 ይህም የሚሆነው የመጨረሻው መለከት ሲነፋ ድንገት በቅጽበተ ዐይን ነው። መለከት ይነፋል፤ ሙታን የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

52 የምንለወጠውም የመጨረሻው እምቢልታ በሚነፋበት ጊዜ እንደ ዐይን ቅጽበት በአንድ ጊዜ ነው። መለከቱ ይነፋል፤ የሞቱትም ሰዎች የማይጠፉ ሕያዋን ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

52 ነገር ግን የኋ​ለ​ኛው መለ​ከት ሲነፋ ሁላ​ችን እንደ ዐይን ጥቅሻ በአ​ንድ ጊዜ እን​ለ​ወ​ጣ​ለን፤ መለ​ከት ይነ​ፋል፤ ሙታ​ንም የማ​ይ​ፈ​ርሱ ሁነው ይነ​ሣሉ፤ እኛም እን​ለ​ወ​ጣ​ለን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 15:52
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

መላእክቱን ከታላቅ መለከት ጋር ይልካቸዋል፤ የእርሱን ምርጦች ከሰማያት ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱ ነፋሳት ይሰበስባሉ።


“እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ሙታን የእግዚአብሔርን ልጅ ድምፅ የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤ እርሱም አሁን ነው፤ የሚሰሙትም በሕይወት ይኖራሉ።


በዚህ አታድንቁ፤ በመቃብር ያሉቱ ሁሉ ድምፁን የሚሰሙበት ሰዓት ይመጣል፤


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ታላቅ መለከት ይነፋል፥ በአሦርም የጠፉ፥ በግብጽ ምድርም የተሰደዱ ይመጣሉ፤ በተቀደሰውም ተራራ በኢየሩሳሌም ለጌታ ይሰግዳሉ።


የጌታ ቀን ግን እንደ ሌባ በድንገት ይመጣል፤ በዚያም ቀን ሰማያት በታላቅ ድምፅ ያልፋሉ፤ ምድርም በእርሷም ላይ የተደረገው ሁሉ ይቃጠላል።


የሙታን ትንሣኤም እንደዚሁ ነው፤ የሚበሰብስ አካል ይዘራል፤ የማይበሰብስ አካል ሆኖ ይነሣል፤


ጌታም በእነርሱ ላይ ይገለጣል፥ የአምላኩም ቀስት እንደ መብረቅ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ጌታም መለከትን ይነፋል፥ ከደቡብም ዐውሎ ነፋስ ይመጣል።


አየሁም፤ አንድም ንስር በሰማይ መካከል እየበረረ በታላቅ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “የቀሩት ሦስቱ መላእክት መለከትን በሚነፋበት ጊዜ ከሚቀረው ድምፅ የተነሣ በምድር ላይ ለሚኖሩት ወዮላቸው! ወዮላቸው! ወዮላቸው!”


ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እነግራችኋለሁ፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ የሚጠፋውም የማይጠፋውን አይወርስም።


በእግዚአብሔርም ፊት የሚቆሙትን ሰባቱን መላእክት አየሁ፤ ሰባትም መለከት ተሰጣቸው።


ዘበኛው ግን ሰይፍ ሲመጣ አይቶ መለከቱን ባይነፋ፥ ሕዝቡን ባያስጠነቅቅ፥ ሰይፍም መጥቶ አንድ ሰው ከእነርሱ ቢወስድ፥ እርሱ በኃጢአቱ ተወስዶአል ደሙን ግን ከዘበኛው እጅ እፈልጋለሁ።


እናንት በዓለም ውስጥ ያላችሁና በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሆይ፥ ምልክት በተራሮች ላይ በሚወጣ ጊዜ ተመልከቱ! መለከትም በተነፋ ጊዜ ስሙ!


እንዲህም ሆነ በሦስተኛው ቀን ማለዳ ነጎድጓድ፥ መብረቅና ከባድ ደመና እጅግም የበረታ የቀንደ መለከት ድምጽ በተራራው ላይ ሆነ፤ በሰፈሩ የነበሩት ሕዝብ ሁሉ ተንቀጠቀጡ።


እርሱም በምድሪቷ ላይ ሰይፍ ሲመጣ አይቶ መለከትን ቢነፋ ሕዝቡንም ቢያስጠነቅቅ፥


እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ፥ በድንጋጤ ጠፉ።


ሕዝቡም ሁሉ ነጎድጓዱንና መብረቁን፥ የቀንደ መለከቱን ድምፅ፥ ተራራውንም ሲጤስ አዩ፤ ሕዝቡም ፈሩ ተንቀጠቀጡም፥ ርቀውም ቆሙ።


አንዱን መለከት ብቻ ቢነፉ ግን ታላላቆቹ የእስራኤል ነገድ አለቆች በአንተ ዘንድ ይሰብሰቡ።


ጌታም ሙሴን፦ “ለእስራኤል ልጆች ‘እናንተ አንገተ ደንዳና ሕዝብ ናችሁ፥ አንድ ጊዜ ከእናንተ ጋር ብወጣ አጠፋችኋለሁ፤ አሁንም በእናንተ ላይ የማደርገውን እንዳውቅ ጌጣችሁን አውጡ’ በላቸው አለው።”


“ከዚህ ማኅበር መካከል ርቃችሁ ገለል በሉ፥ እኔም በአንድ ጊዜ አጠፋቸዋለሁ።” በግምባራቸውም ወድቀው ሰገዱ።


“ሁሉንም በአንድ ጊዜ ስለማጠፋቸው ከዚህ ማኅበር መካከል ተለዩ።”


ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ተራ ይሆናል፤ መጀመሪያ በኵራት የሆነው ክርስቶስ፥ በኋላም ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜ የእርሱ የሆኑት።


በጌታ ቃል ይህን እንላችኋለን፤ እኛ ሕያዋን የሆንነው፥ ጌታም እስኪመጣ ድረስ የምንቀረው ያንቀላፉቱን አንቀድምም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች