Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 14:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እንግዲህ የሚነገረውን ቋንቋ ትርጉሙን ካላወቅሁ፥ ለተናጋሪው እንግዳ እሆንበታለሁ፤ እርሱም ለእኔ እንግዳ ይሆንብኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እንግዲህ አንድ ሰው የሚናገረውን ቋንቋ ትርጕሙን ካላወቅሁ፣ ለሚናገረው እንግዳ እሆንበታለሁ፤ እርሱም ለእኔ እንግዳ ይሆንብኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 እንግዲህ እኔ የሚነገረውን ቋንቋ ትርጒም የማላውቅ ብሆን ለተናጋሪው ሰው እንግዳ እሆናለሁ፤ እርሱም ለእኔ እንግዳ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የቋ​ን​ቋ​ውን ትር​ጓሜ ካላ​ወ​ቅሁ እኔ ለሚ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ረኝ እንደ እን​ግዳ እሆ​ን​በ​ታ​ለሁ፤ የሚ​ያ​ነ​ጋ​ግ​ረኝ እር​ሱም ለእኔ እንደ እን​ግዳ ይሆ​ናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እንግዲህ የቋንቋውን ፍች ባላውቅ ለሚናገረው እንግዳ እሆናለሁ፥ የሚናገረውም ለእኔ እንግዳ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 14:11
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አረማውያንም የሚያስገርም ቸርነት አደረጉልን፤ ዝናብ ስለ ሆነም ስለ ብርዱም እሳት አንድደው ሁላችንን ተቀበሉን።


በዚህም መታደስ ግሪካዊና አይሁዳዊ፥ የተገረዘና ያልተገረዘ፥ አረማዊና እስኩቴስ፥ ባርያና ነጻ ሰው የሚባል ነገር አይኖርም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፤ በሁሉም ነው።


“ቋንቋቸው እንግዳ በሆነ ሰዎች፥ በባዕዳንም አንደበት ለዚህ ሕዝብ እናገራለሁ፤ ይህም ሆኖ አይሰሙኝም፥ ይላል ጌታ” ተብሎ በኦሪትም ተጽፎአል።


ለግሪኮችና ግሪኮች ላልሆኑት፥ ለጥበበኞችና ለማያስተውሉትም ዕዳ አለብኝ፤


አረማውያንም እባብ በእጁ ተንጠልጥላ ባዩ ጊዜ፥ እርስ በርሳቸው “ይህ ሰው በእርግጥ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ከባሕርም ስንኳ በደኅና ቢወጣ የእግዚአብሔር ፍርድ በሕይወት ይኖር ዘንድ አልተወውም፤” አሉ።


በዓለም ላይ ብዙ ዓይነት ቋንቋዎች አሉ፤ ትርጒም የሌለውም ቋንቋ የለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች