Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 14:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፥ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ፍቅርን ተከታተሉ፤ መንፈሳዊ ስጦታዎችን፣ በተለይም ትንቢት የመናገርን ስጦታ በብርቱ ፈልጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 እንግዲህ ፍቅርን ተከታተሉ፤ የመንፈስ ቅዱስ ስጦታዎችን ይልቁንም ትንቢት የመናገር ስጦታን በብርቱ ፈልጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ፍቅ​ርን ተከ​ተ​ሏት፤ ለመ​ን​ፈ​ሳዊ ስጦታ፥ ይል​ቁ​ንም ትን​ቢት ለመ​ና​ገር ተፎ​ካ​ከሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ፍቅርን ተከታተሉ፥ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 14:1
29 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለዚህ፥ ወንድሞች ሆይ፤ ትንቢት ለመናገር በብርቱ ፈልጉ፤ በልሳን መናገርንም አትከልክሉ፤


ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ለመኖር ጣሩ፤ ያለ ቅድስናም ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና ለመቀደስም ፈልጉ።


ሽማግሌዎች እጃቸውን በአንተ ላይ የጫኑ ጊዜ በትንቢት የተሰጠህን የጸጋ ስጦታ ቸል አትበል።


የምታደርጉትን ሁሉ በፍቅር አድርጉ።


ስለ መንፈሳዊ ነገርም፥ ወንድሞች ሆይ! አላዋቂ እንድትሆኑ አልፈልግም።


እንግዲህ እምነት፥ ተስፋ፥ ፍቅር እነዚህ ሦስቱ ጸንተው ይኖራሉ፤ ከእነዚህም የሚበልጠው ፍቅር ነው።


የኀጥኣን መንገድ በጌታ ዘንድ አስጸያፊ ነው፥ እርሱ ግን ጽድቅን የሚከተል ይወድዳል።


የእግዚአብሔር ሰው ሆይ! አንተ ግን ከእነዚህ ነገሮች ሽሽ፤ ጽድቅን፥ እግዚአብሔርን መምሰልን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ መጽናትን፥ የዋህነትን ግን ተከተል።


ማንም ነቢይ ነኝ የሚል ወይም መንፈሳዊ ሰው ነኝ የሚል ቢኖር፥ ይህ የጻፍሁላችሁ የጌታ ትእዛዝ መሆኑን ይወቅ፤


እናንተ ጽድቅን የምትከተሉ ጌታንም የምትሹ፥ ስሙኝ፤ ከእርሱ የተቈረጣችሁበትን ዐለት ከእርሱም የተቈፈራችሁበትን ጉድጓድ ተመልከቱ።


እንዲሁም ልጆችን በማሳደግ፥ እንግዶችንም በመቀበል፥ የቅዱሳንንም እግሮች በማጠብ፥ የተጨነቁትንም በመርዳት፥ በበጎም ሥራ ሁሉ በመትጋት፥ በመልካም ሥራዎችዋ የተመሰከረላት ልትሆን ይገባል።


በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


ነገር ግን የላቀውን የጸጋ ስጦታ በብርቱ ፈልጉ። ደግሞም ከሁሉ የሚበልጥ መንገድ አሳያችኋለሁ።


ጽድቅንና ምሕረትን የሚከተል ሕይወትንና ጽድቅን ክብርንም ያገኛል።


ወዳጄ ሆይ! መልካሙን እንጂ ክፉን አትምሰል። መልካም የሚያደርግ ከእግዚአብሔር ነው ክፉን የሚያደርግ ግን እግዚአብሔርን አላየውም።


እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችነት መዋደድ፥ በወንድማማችነትም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።


እንደ ተሰጠንም ጸጋ መጠን የተለያዩ ስጦታዎች አሉን፤ ትንቢት ከሆነ እንደ እምነት መጠን መናገር፤


ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፤ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን፥ እምነትን፥ ፍቅርን፥ ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።


እንግዲህ ምን እንላለን? አሕዛብ ጽድቅን ሳይከተሉ ጽድቅን አገኙ፤ እርሱም በእምነት የሆነ ጽድቅ ነው፤


እንግዲህ የሰላም ነገርና እርስ በርሳችንም የምንታነጽበትን ነገር እንከተል።


ከዚያ በኋላ የፍልስጥኤማውያን ጦር ወዳለበት ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወደ ጊብዓ ትሄዳለህ። ወደ ከተማዪቱ እንደ ደረስክም የነቢያት ጉባኤ በበገና፥ በከበሮ፥ በዋሽንትና በመሰንቆ ታጅበው ትንቢት እየተናገሩ ከማምለኪያው ኰረብታ ላይ ሲወርዱ ታገኛቸዋለህ።


ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።


በዚህ ዓይነት፥ በልሳን መናገር ለማያምኑ የሚሆን ምልክት እንጂ ለሚያምኑት አይደለም፤ ትንቢት ግን ለሚያምኑ እንጂ ለማያምኑ አይደለም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች