Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 12:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋል፤ ለሌላውም ያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ለአንዱ በመንፈስ የጥበብን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤ ለሌላው ደግሞ በዚያው መንፈስ የዕውቀትን ቃል መናገር ይሰጠዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 መንፈስ ቅዱስ ለአንዱ ሰው በጥበብ የመናገር ችሎታን ይሰጠዋል፤ ለሌላው ሰው ደግሞ ያው መንፈስ በዕውቀት የመናገርን ችሎታ ይሰጠዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጥ​በብ ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ፤ በመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስም የዕ​ው​ቀት ቃል የሚ​ሰ​ጠው አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 12:8
30 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እንዲያስተምራቸው መልካሟን መንፈስህን ሰጠሃቸው፥ መናህን ከአፋቸው አልከለከልክም፥ ለጥማታቸውም ውኃን ሰጠሃቸው።


ነገር ግን በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ማስተዋልን ይሰጣል።


አንተ አምላኬ ነህና ፈቃድህን ለማድረግ አስተምረኝ፥ ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ ምድር ይምራኝ።


በጥበብ፥ በማስተዋል፥ በእውቀትና ሥራ ሁሉ እንዲሠራ የእዚአብሔርን መንፈስ ሞላሁበት፥


ጌታ ጥበብን ይሰጣልና፥ ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ፥


የደከመውን በቃል እንዴት እንደምደግፍ እንዳውቅ ጌታ እግዚአብሔር የተማሩትን ምላስ ሰጥቶኛል፤ ማለዳ ማለዳ ያነቃኛል፥ እንደ ተማሪዎችም እንድትሰማ ጆሮዬን ያነቃቃል።


ከእነርሱ ጋር ያለው ቃል ኪዳኔ ይህ ነው ይላል ጌታ፤ በአንተ ላይ ያለው መንፈሴ በአፍህም ውስጥ ያደረግሁት ቃሌ ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ድረስ ከአፍህ፥ ከዘርህም አፍ፥ ከዘር ዘርህም አፍ አይለይም፥ ይላል ጌታ።


እርሱም እንዲህ ሲል መለሰላቸው “ለእናንተ የመንግሥተ ሰማያትን ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቶአችኋል፤ ለእነርሱ ግን አልተሰጣቸውም።


ወንድሞች ሆይ! በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፤ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤


ወንድሞቼ ሆይ! እኔም ራሴ ስለ እናንተ በበጎነት ራሳችሁ እንደ ተሞላችሁ፥ እውቀትም ሁሉ እንደ ሞላባችሁ፥ እርስ በርሳችሁም ደግሞ ልትወቃቀሱ እንደምትችሉ ተረድቼአለሁ።


ከእግዚአብሔር ዘንድ ጥበባችን፥ ጽድቃችንና ቅድስናችንም ቤዛችንም በተደረገልን፥ በክርስቶስ ኢየሱስ የሆናችሁ ከእርሱ ነው።


በንግግር ሁሉ በእውቀትም ሁሉ በሁሉም ነገር በእርሱ ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ተደርጋችኋልና፤


ትንቢት የመናገር ስጦታ ቢኖረኝ፥ ምስጢርን ሁሉ ባውቅ፥ ዕውቀትን ሁሉ ብረዳ፥ ተራሮችንም እስካፈልስ ድረስ እምነት ሁሉ ቢኖረኝ ፍቅር ግን ከሌለኝ ከንቱ ነኝ።


ፍቅር ከቶ አይወድቅም፤ ትንቢት የመናገር ስጦታም ቢሆን ይሻራል፤ ልሳንም ቢሆን ይቀራል፤ ዕውቀትም ቢሆን ያልፋል።


ወንድሞች ሆይ፤ እንግዲህ ምን እንበል? በምትሰበሰቡበት ጊዜ እያንዳንዱ መዝሙር አለው፤ ትምህርት አለው፤ መግለጥ አለው፤ በልሳን መናገር አለው፤ መተርጐም አለው። ይህ ሁሉ ግን ለማነጽ ይሁን።


እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ ወደ እናንተ በምመጣበት ጊዜ በልሳኖች ብናገር፥ በመግለጥ፥ በእውቀት ወይም በትንቢት ወይም በትምህርት ካልነገርኩአችሁ ምን እጠቅማችሃለሁ?


በእርሱ ውስጥ ካለው ከሰው መንፈስ በቀር የሰውን ነገር የሚያውቅ ሰው ማን ነው? እንዲሁም ደግሞ ከእግዚአብሔር መንፈስ በቀር የእግዚአብሔርን ነገር ማንም አያውቅም።


ሊመክረውስ የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው? እኛ ግን የክርስቶስ ልቦና አለን።


ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።


በአነጋገሬ ያልተማርሁ ብሆን እንኳ፥ በእውቀት ግን እንዲህ አይደለሁም። ነገር ግን በሰው ሁሉ መካከል ይህንን ግልጽ አድርገንላችኋል።


ነገር ግን በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን፥ በእኛም በሁሉም ስፍራ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ፥ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።


በክርስቶስ ፊት የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት እንዲሰጥ ብርሃን በልባችን ውስጥ ያበራ፥ “በጨለማ ብርሃን ይብራ፤” ያለው እግዚአብሔር ነው።


በንጽሕና፥ በእውቀት፥ በትዕግሥት፥ በቸርነት፥ በመንፈስ ቅዱስ፥ በእውነተኛ ፍቅር፥


ነገር ግን በነገር ሁሉ፥ በእምነት፥ በቃል፥ በእውቀት፥ በትጋት፥ እንዲሁም ለእኛ በፍቅራችሁ ልቃችሁ እንደተገኛችሁ፥ በዚህ ቸር ሥራ ደግሞ ልቃችሁ ተገኙ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች