1 ቆሮንቶስ 10:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)33 እኔ ደግሞ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ ነገር ግን ብዙዎቹ እንዲጠቀሙ፥ በሁሉ ነገር ሰውን ሁሉ ደስ ለማሰኘት የምጥረው፥ ይድኑ ዘንድ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም33 እኔ ሰውን ሁሉ በማንኛውም ረገድ ለማስደሰት እንደምጥር እናንተም እንዲሁ አድርጉ፤ ብዙዎችም ይድኑ ዘንድ፣ ለራሴ የሚጠቅመውን ሳይሆን ለእነርሱ የሚጠቅመውን እሻለሁና። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም33 እኔ ሁሉም እንዲድኑ የሌሎችን ጥቅም እንጂ የራሴን ጥቅም ሳልፈልግ ሰውን ሁሉ በማደርገው ነገር ሁሉ እንደማስደስት እናንተም እንዲሁ አድርጉ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)33 እኔም ሁሉን በሁሉ ነገር ደስ እንዳሰኝ ይድኑ ዘንድ የብዙዎችን ተድላ እሻለሁ እንጂ የራሴን ተድላ የምሻ አይደለሁምና። ምዕራፉን ተመልከት |