Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 10:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ይህ ሁሉ ነገር እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፤ የተጻፈው ግን በዘመናት መጨረሻ ለምንገኘው ለእኛ ተግሣጽ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ይህ ሁሉ ምሳሌ ይሆን ዘንድ በእነርሱ ላይ ደረሰ፤ የዘመናት ፍጻሜ የደረሰብንን እኛን ለማስጠንቀቅም ተጻፈ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ይህ ሁሉ ነገር የደረሰባቸው ለእኛ የማስጠንቀቂያ ምሳሌ እንዲሆን ነው፤ የተጻፈውም በዘመናት መጨረሻ ላይ ለምንገኘው ለእኛ ትምህርት እንዲሆነን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነ​ር​ሱን ያገ​ኛ​ቸው ይህ ሁሉ ነገር በኋላ ዘመን ለም​ን​ነ​ሣው ለእኛ ትም​ህ​ር​ትና ምክር ሊሆ​ነን ምሳሌ ሆኖ ተጻፈ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው፥ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገሥጸን ተጻፈ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 10:11
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አባታቸውንም በዚያች ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ አጠጡት፥ ታናሺቱም ገብታ ከእርሱ ጋር ተኛች፥ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም።


ወደ ችግረኞች ጸሎት ተመለከተ፥ ልመናቸውንም አልናቀም።


በአንቺ ላይ በንዴትና በቁጣ፥ በመዓትም ዘለፋ ፍርድን ባደረግሁብሽ ጊዜ፥ በዙሪያሽ ላሉ አገሮች መሰደቢያና መተረቻ፥ ማስጠንቀቂያና ድንጋጤ ትሆኛለሽ፥ እኔ ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።


የዘራው ጠላት ደግሞ ዲያብሎስ ነው፤ መከሩም የዓለም መጨረሻ ነው፤ አጫጆቹ መላእክት ናቸው።


እንግዲህ እንክርዳድ ተለቅሞ በእሳት እንደሚቃጠል ሁሉ በዓለም መጨረሻም እንዲሁ ይሆናል።


እንግዲህ ከእንቅልፍ የምትነቁበት ሰዓት ጊዜው አሁን መሆኑን እወቁ፤ ካመንንበት ጊዜ ይልቅ አሁን መዳናችን ወደ እኛ ቀርቧልና።


ሌሊቱ አልፎአል፤ ቀኑም ቀርቧል፤ እንግዲህ የጨለማውን ሥራ አውጥተን የብርሃንን የጦር መሣሪያ እንልበስ።


በመጽናትና መጻሕፍት በሚሰጡት መጽናናት ተስፋ ይሆንልን ዘንድ አስቀድሞ የተጻፈው ነገሮች ሁሉ ለትምህርታችን ተጽፎአል።


ነገር ግን “ተቆጠረለት” የሚለው ቃል የተጻፈው በእርሱ ምክንያት ብቻ አይደለም፤


እነርሱ ክፉ ነገር እንደ ተመኙ እኛም እንዳንመኝ እነዚህ ነገሮች ምሳሌ ሆኑልን።


ዳሩ ግን ወንድሞች ሆይ! ይህን እናገራለሁ፤ ዘመኑ አጭር ሆኖአል፤ ከእንግዲህ ወዲህ ሚስቶች ያሉአቸው እንደሌላቸው ይሁኑ፤


ይህን የሚለው ፈጽሞ ስለ እኛ አይደለምን? በእርግጥ ስለ እኛ ተጽፎአል፥ ይኸውም የሚያርስ በተስፋ እንዲያርስ፥ የሚያበራይም እንዲካፈል በተስፋ ሊያበራይ ስለሚገባው ነው።


እነዚህም ምሳሌዎች ናቸው፤ እነዚህም ሁለቱ ኪዳኖች ናቸውና፥ አንደኛዋ ከሲና ተራራ ልጆችን ለባርነት ትወልዳለች፥ እርሷም አጋር ናት።


ገርነታችሁ ለሰው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ መምጫው ቀርቦአል።


አንዳንዶችም ልምድ አድርገው እንደያዙት፥ መሰብሰባችንን አንተው፤ እርስ በርሳችን እንመካከር፤ ይልቁንም የቀኑን መቅረብ እያያችሁ አብልጣችሁ ይህን አድርጉ።


ምክንያቱም ገና “በጣም ጥቂት ጊዜ፥ ሊመጣ ያለውም ይመጣል፥ አይዘገይምም፤


ልጆች ሆይ፥ ይህ የመጨረሻው ሰዓት ነው፤ የክርስቶስ ተቃዋሚ ይመጣል ሲባል እንደ ሰማችሁት አሁን እንኳ ብዙ የክርስቶስ ተቃዋሚዎች መጥተዋል፤ በዚህም ይህ የመጨረሻው ሰዓት እንደሆነ እናውቃለን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች