1 ዜና መዋዕል 28:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)1 ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የሠራዊቱ አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሥና በልጆቹ ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኃያላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም1 ዳዊት በኢየሩሳሌም እንዲሰበሰቡ የነገዱን የጦር አለቆች፣ ንጉሡን የሚያገለግሉትን የከፍለ ጦር አዛዦች፣ የሻለቆቹን፣ የመቶ አለቆቹን፣ የንጉሡና የልጆቹ ንብረትና ከብት ሁሉ ኀላፊ የሆኑትን፣ እንዲሁም የቤተ መንግሥቱን ሹማምት፣ ኀያላንና ጀግና ተዋጊዎቹን፣ በአጠቃላይ የእስራኤልን ሹማምት ሁሉ ጠራ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም1 ንጉሥ ዳዊት የእስራኤል ባለ ሥልጣኖች በሙሉ ወደ ኢየሩሳሌም መጥተው እንዲሰበሰቡ ትእዛዝ አስተላለፈ፤ ስለዚህ የየነገዱ መሪዎች፥ የመንግሥቱን ሥራ የሚያካሂዱ ባለሥልጣኖች የሻአለቆችና የመቶ አለቆች፥ የንጉሡንና የወንዶች ልጆቹን ንብረትና የቀንድ ከብት ተቈጣጣሪዎች እንዲሁም የቤተ መንግሥት ባለሟሎች፥ ዝነኞችና ታዋቂ የሆኑ ጀግኖች ሰዎች በሙሉ በኢየሩሳሌም ተሰበሰቡ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)1 ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉና የፍርድ አለቆችን፥ ንጉሡንም በየተራ የሚጠብቁትን አለቆቹን፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሡና በልጆቹ ሀብትና ንብረት ላይ፥ መባ ባለበት ላይ የተሾሙትን ጃንደረቦችንም፥ ኀያላኑንና ሰልፈኞቹን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)1 ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉ፥ የነገዶቹንም አለቆች፥ ንጉሡንም በክፍል የሚያገለግሉትን የጭፍሮች አለቆች፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሥና በልጆች ሀብትና ግዛት ላይ የተሾሙትን፥ ጃንደረቦችንም፥ ጽኑዓን ኀያላኑንም ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ። ምዕራፉን ተመልከት |