1 ዜና መዋዕል 26:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ለልጁም ለሸማያ ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ ጽኑዓንም ኃያላን ነበሩና በአባታቸው ቤት ሠለጠኑ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6-7 የዖቤድኤዶም የበኲር ልጅ ሸማዕያ ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ዖትኒ፥ ረፋኤል፥ ዖቤድ፥ ኤልዛባድ ኤሊሁና ሰማክያ ተብለው የሚጠሩት ናቸው፤ እነርሱም ስለ ነበራቸው ታላቅ ችሎታ በጐሣቸው መሪዎች ነበሩ፤ በተለይ የመጨረሻዎቹ ሁለቱ ከፍ ያለ ችሎታ ነበራቸው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 ለልጁ ለሰማያም ከበኵር ልጁ ከሮሲ ልጆች ተወለዱለት፤ እነርሱም በአባታቸው ቤት የሠለጠኑ እጅግም ኀያላን ነበሩ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 ለልጁም ለሸማያ ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ ጽኑዓንም ኀያላን ነበሩና በአባታቸው ቤት ሠለጠኑ። ምዕራፉን ተመልከት |