1 ዜና መዋዕል 24:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)19 የእስራኤል አምላክ ጌታ እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዓት ወደ ጌታ ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዓት ይህ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም19 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ባዘዘውና ከቀድሞ አባታቸው ከአሮን በተሰጣቸው መመሪያ መሠረት ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ በሚገቡበት ጊዜ፣ የተወሰነላቸው ሥርዐት ይህ ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም19 እነዚህም ሰዎች የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር የቀድሞ አባታቸውን አሮንን ባዘዘው መሠረት ወደ ቤተ መቅደስ ገብተው የሥራ ድርሻቸው ክፍፍል ይህ ነው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ በአባታቸው በአሮን እጅ እንደ ተሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት ይገቡ ዘንድ እንደ እየአገልግሎታቸው ቍጥራቸው ይህ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)19 የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዳዘዘ፥ አባታቸው አሮን እንደሰጣቸው ሥርዐት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚገቡበት የአገልግሎታቸው ሥርዐት ይህ ነበረ። ምዕራፉን ተመልከት |