Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 21:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 የጌታም መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ላይ ለጌታ መሠዊያ እንዲሠራ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚያም የእግዚአብሔር መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 የእግዚአብሔር መልአክ ጋድን “ዳዊት ወደ ኢያቡሳዊው ወደ ኦርና አውድማ ሄዶ ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንዲሠራ ንገረው” አለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መል​አክ ዳዊት ወጥቶ በኢ​ያ​ቡ​ሳ​ዊው በኦ​ርና አው​ድማ ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ ይሠራ ዘንድ ለዳ​ዊት እን​ዲ​ነ​ግ​ረው ጋድን አዘ​ዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 የእግዚአብሔርም መልአክ ዳዊት ወጥቶ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ ላይ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራ ዘንድ ለዳዊት እንዲነግረው ጋድን አዘዘው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 21:18
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ቀን ጋድ ወደ ዳዊት መጥቶ፥ “ውጣና በኢያቡሳዊው በኦርና ዐውድማ ላይ ለጌታ መሠዊያ ሥራ” አለው።


ጋድም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘የምትወድደውን ምረጥ፤


እግዚአብሔርም ለማጥፋት ወደ ኢየሩሳሌም መልአክን ላከ፤ ሊያጠፋትም በቀረበ ጊዜ ጌታ አይቶ ስለ ክፉው ነገር ተፀፀተ፥ የሚያጠፋውንም መልአክ፦ “በቃህ፤ አሁን እጅህን መልስ” አለው። የጌታም መልአክ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ አጠገብ ቆሞ ነበር።


ዳዊትም በጌታ ስም እንደ ተናገረው እንደ ጋድ ቃል ወጣ።


ዳዊትም፦ “ይህ የጌታ የእግዚአብሔር ቤት ነው፥ ይህም ለእስራኤል የሚቃጠለው መሥዋዕት የሚቀርብበት መሠዊያ ነው” አለ።


ሰሎሞንም ጌታ ለአባቱ ለዳዊት በተገለጠበት በሞሪያ ተራራ ዳዊት ባዘጋጀው ስፍራ በኢያቡሳዊው በኦርና አውድማ በኢየሩሳሌም የጌታን ቤት መሥራት ጀመረ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች