1 ዜና መዋዕል 19:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)3 የአሞን ልጆች ሹማምንት ግን ሐኖንን እንዲህ አሉት፦ “ዳዊት አባትህን አክብሮ የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ባርያዎቹስ አገሪቱን ለመመርመር፥ ለማጥፋት፥ ለመሰለልም ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም3 የአሞናውያን መኳንንት ለሐኖን፣ “ዳዊት ሐዘኑን ለመግለጽ ሰዎችን ወደ አንተ የላከው አባትህን አክብሮ ይመስልሃልን? ሰዎቹ ወደ አንተ የመጡት አገሪቱን ለመመርመር፣ ለመሰለልና ለመያዝ አይደለምን?” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም3 ዐሞናውያን ባለሥልጣኖች ንጉሡን እንዲህ አሉት፤ “ዳዊት እነዚህን ሰዎች የላከው አባትህን በማክበር የሐዘንህ ተካፋይ ለመሆን ይመስልሃልን? ከቶ እንዳይመስልህ! እርሱ እነዚህን መልእክተኞች የላከው ምድሪቱን ወሮ መያዝ ይችል ዘንድ እንዲሰልሉለት ነው።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 የአሞን ልጆች አለቆች ግን ሐናንን፥ “ዳዊት የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ አባትህን በማክበር ነውን? አገልጋዮቹስ ከተማዪቱን ለመመርመርና ሀገሪቱንም ለመሰለል ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?” አሉት። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)3 የአሞን ልጆች አለቆች ግን ሐኖንን “ዳዊት አባትህን አክብሮ የሚያጽናኑህን ወደ አንተ የላከ ይመስልሃልን? ባሪያዎቹስ አገሪቱን ለመመርመር፥ ለማጥፋት፥ ለመሰለልም ወደ አንተ የመጡ አይደሉምን?” አሉት። ምዕራፉን ተመልከት |