Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 19:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት ሺህ ሰረገለኞች፥ አርባ ሺህም እግረኞች ገደለ፥ የሠራዊቱንም አለቃ ሾፋክን ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ። ዳዊትም ሰባት ሺሕ ሠረገለኞችና አርባ ሺሕ እግረኛ ወታደሮች ገደለ። የሰራዊታቸው አዛዥ ሾፋክም በጦርነቱ ላይ ሞተ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 እስራኤላውያንም ሶርያውያንን ወደ ኋላ መልሰው አባረሩአቸው፤ ዳዊትና ሠራዊቱ ሰባት ሺህ ሠረገላ ነጂዎችን፥ አርባ ሺህ እግረኛ ወታደሮችን ገደሉ፤ እንዲሁም ሾባክ ተብሎ የሚጠራውን የሶርያውያንን የጦር አዛዥ ገደሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ሶር​ያ​ው​ያ​ንም ከዳ​ዊት ፊት ሸሹ፤ ዳዊ​ትም ከሶ​ር​ያ​ው​ያን ሰባት ሺህ ሰረ​ገ​ለ​ኞ​ችን፥ አርባ ሺህም እግ​ረ​ኞ​ችን ገደለ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ሶፋ​ክን ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት ሺህ ሠረገለኞች፥ አርባ ሺህም እግረኞች ገደለ፤ የሠራዊቱንም አለቃ ሾፋክን ገደለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 19:18
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ይሁን እንጂ ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ሰባት መቶ ሠረገለኞችንና አርባ ሺህ ፈረሰኞችን ገደለባቸው። እንዲሁም የሠራዊታቸውን አዛዥ ሾባክን አቁስሎት ስለ ነበር እዚያው ሞተ።


ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም በሶርያውያን ላይ ለውግያ በተሰለፈ ጊዜ እነርሱ ከእርሱ ጋር ተዋጉ።


የአድርአዛርም ባርያዎች በእስራኤል ፊት እንደ ተሸነፉ ባዩ ጊዜ ከዳዊት ጋር ታረቁ፥ ገበሩለትም፤ ሶርያውያንም ከዚያ ወዲያ የአሞንን ልጆች ለመርዳት እንቢ አሉ።


ከጌታ በቀር አምላክ ማን ነው? ከአምላካችን በቀር አምላክ ማን ነው?


ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት አይድንም፥ ኃያልም በጉልበቱ አያመልጥም።


ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች