1 ዜና መዋዕል 19:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 አይዞህ፥ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ ጌታም ደስ ያሰኘውን ያድርግ።” ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እንግዲህ በርቱ፤ ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተሞች በጀግንነት እንዋጋ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሠኘውን ያድርግ።” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እንግዲህ አይዞህ በርታ! ለሕዝባችንና ለአምላካችን ከተማዎች ስንል በርትተን እንዋጋ፤ ለዚህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 አይዞህ፥ በርታ፤ ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ እግዚአብሔርም በፊቱ ደስ ያሰኘውን ያድርግ” አለ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 አይዞህ! ስለ ሕዝባችንና ስለ አምላካችንም ከተሞች እንበርታ፤ እግዚአብሔርም ደስ ያሰኘውን ያድርግ፤” አለ። ምዕራፉን ተመልከት |