Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 17:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 አምላኬ ሆይ! ቤት እንደምትሠራለት ለባርያህ ገልጠህለታልና ስለዚህ ባርያህ ወደ አንተ ለመጸለይ በልቡ ደፈረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 “አምላኬ ሆይ፤ ቤት እንደምትሠራለት ለባሪያህ ገልጸህለታል፤ ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ለመጸለይ ድፍረት አገኘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 አምላኬ ሆይ፥ አንተ ለእኔ ለባሪያህ ቤትን እንደምትሠራልኝ ስለ ገለጥክልኝ ይህን ጸሎት ለማቅረብ ድፍረት አገኘሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 አም​ላኬ ሆይ፥ ቤት እን​ድ​ት​ሠ​ራ​ለት ለባ​ሪ​ያህ በጆሮው ገል​ጠ​ሃ​ልና ስለ​ዚህ አገ​ል​ጋ​ይህ ወደ አንተ ይጸ​ልይ ዘንድ ባለ​ሟ​ል​ነ​ትን አገኘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 አምላኬ ሆይ! ቤት እንድትሠራለት ለባሪያህ ገልጠሃልና ስለዚህ ባሪያህ ወደ አንተ ይጸልይ ዘንድ በልቡ ደፈረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 17:25
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስምህ፦ ‘የሠራዊት ጌታ እርሱ የእስራኤል አምላክ ነው፥ በእውነት የእስራኤል አምላክ ነው’ በሚለው ውስጥ ለዘለዓለም ጽኑና ታላቅ ይሆናል፤ የባርያህም የዳዊት ቤት በፊትህ ጸንቶአል።


አሁንም፥ አቤቱ፥ አንተ አምላክ ነህ፥ ይህንም መልካም ነገር ለባርያህ ተናግረሃል።


ጌታ ሆይ የምስኪኖችን ምኞት ሰማህ፥ ልባቸውንም ታጸናለህ፥ ጆሮህንም ታዘነብላለህ፤


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ አሁንም የእስራኤል ቤት እንድሠራላቸው እንዲፈልጉኝ እፈቅድላቸዋለሁ፥ ሰዎችንም እንደ መንጋ አበዛላቸዋለሁ።


ሳኦል ከመምጣቱ ከአንድ ቀን በፊት ጌታ ለሳሙኤል እንዲህ ሲል ገልጦለት ነበር፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች