Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 17:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን፦ “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የጌታም ቃል ኪዳን ታቦት በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ዳዊት በቤተ መንግሥቱ ተደላድሎ በተቀመጠበት ጊዜ፣ ነቢዩ ናታንን “እነሆ፤ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤተ መንግሥት ውስጥ እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የኪዳኑ ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ይኖራል” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ንጉሥ ዳዊት በዚህ ጊዜ በቤተ መንግሥቱ ነበር፤ አንድ ቀን ንጉሡ ነቢዩን ናታንን አስጠርቶ “እነሆ እኔ ከሊባኖስ ዛፍ እንጨት በተሠራ ቤት እኖራለሁ፤ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት ግን በድንኳን ውስጥ ተቀምጦአል!” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተ​ቀ​መጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩ ናታ​ንን፥ “እነሆ፥ ከዝ​ግባ በተ​ሠራ ቤት ተቀ​ም​ጫ​ለሁ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት ግን በመ​ጋ​ረ​ጃ​ዎች ውስጥ ተቀ​ም​ጣ​ለች” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 እንዲህም ሆነ፤ ዳዊት በቤቱ በተቀመጠ ጊዜ ዳዊት ነቢዩን ናታንን “እነሆ፥ እኔ ከዝግባ በተሠራ ቤት ተቀምጫለሁ፤ የእግዚአብሔርም ቃል ኪዳን ታቦት በመጋረጃዎች ውስጥ ተቀምጦአል፤” አለው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 17:1
28 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እስራኤልን ካወጣሁበት ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ ከድንኳን ወደ ድንኳን፥ ከማደሪያም ወደ ማደሪያ እሄድ ነበር እንጂ በቤት ውስጥ አልኖርሁምና።


ዳዊትም በራሱ ከተማ ላይ ለራሱ ቤቶችን ሠራ፤ ለእግዚአብሔርም ታቦት ስፍራ አዘጋጀ፥ ድንኳንም ተከለለት።


እናንተ ብዙ ነገርን ፈልጋችሁ፥ እነሆ ጥቂት ሆነ፤ ወደ ቤትም ባገባችሁት ጊዜ እፍ አልሁበት። በምን ምክንያት? ይላል የሠራዊት ጌታ። ምክንያቱም እናንተ ሁሉ ወደ እየቤታችሁ እየሮጣችሁ የእኔ ቤት ስለፈረሰ ነው።


ይህ ቤት ፈርሶ ሳለ እናንተ ራሳችሁ በታጠሩ ቤቶቻችሁ ለመኖር ጊዜው ነውን?


በዝግባ እንጨት ስለምትወዳደር በውኑ ትነግሣለህን? በውኑ አባትህ ይበላና ይጠጣ ፍርድንና ጽድቅን ያደርግ አልነበረምን? በዚያም ጊዜ መልካም ሆኖለት ነበር።


ለጌታ ስፍራ፥ ለያዕቆብ ኀያል ማደሪያ እስካገኝ ድረስ ብሎ።


ለጌታ ታቦት ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ድንኳን ተክሎለት ነበርና ዳዊት ከቂርያት-ይዓሪም ወዳዘጋጀለት ስፍራ ታቦቱን አምጥቶት ነበር።


የንጉሡም የዳዊት የፊተኛውና የኋለኛው ነገር፥ እነሆ፥ በባለ ራእዩ በሳሙኤል ታሪክ፥ በነቢዩም በናታን ታሪክ፥ በባለ ራእዩም በጋድ ታሪክ ተጽፎአል።


የእግዚአብሔርንም ታቦት ይዘው ገቡ፥ ዳዊትም በተከለለት ድንኳን ውስጥ አኖሩት፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የአንድነቱን መሥዋዕትም በጌታ ፊት አቀረቡ።


የጢሮስም ንጉሥ ኪራም ለዳዊት ቤት እንዲሠሩለት መልእክተኞችን የዝግባ እንጨትንም ጠራቢዎችንም አናጢዎችንም ወደ ዳዊት ላከ።


ንጉሡም ከእርሱ ጋር ካህኑን ሳዶቅንና ነቢዩን ናታንን የዮዳሄንም ልጅ በናያስን ከሊታውያንንና ፈሊታውያንንም ላከ፥ በንጉሡም በቅሎ ላይ አስቀመጡት።


ለንጉሡም፦ “እነሆ፥ ነቢዩ ናታን መጥቷል” ብለው ነገሩት፥ እርሱም ወደ ንጉሡ ፊት በገባ ጊዜ በግምባሩ በምድር ላይ ተደፍቶ ለንጉሡ እጅ ነሣ።


ነገር ግን ካህኑ ሳዶቅና የዮዳሄ ልጅ በናያ፥ ነቢዩም ናታን፥ ሺምዒና ሬዒ፥ የዳዊትም ተዋጊዎች ከአዶንያስ ጋር አልነበሩም።


ጌታ ሕፃኑን ስለ ወደደም ስሙ ይዲድያ ተብሎ እንዲጠራ በነቢዩ በናታን በኩል ቃል ላከ።


ጌታ ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ እርሱም ወደ ዳዊት መጥቶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱም አንዱ ሀብታም ሲሆን፥ ሌላው ደግሞ ድኻ ነበረ።


ከዚያም የጌታን ታቦት አምጥተው፥ ዳዊት በተከለለት ድንኳን ውስጥ በተዘጋጀለት ስፍራ አኖሩት፤ ዳዊትም የሚቃጠል መሥዋዕትና የሰላም መሥዋዕት በጌታ ፊት አቀረበ።


እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝቶ ለያዕቆብ አምላክ ማደሪያን ያገኝ ዘንድ ለመነ።


“አባቴ ዳዊት ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ቤተ መቅደስን ለመሥራት ዐቅዶ ነበር።


ናታንም ዳዊትን፦ “እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና በልብህ ያለውን ሁሉ አድርግ” አለው።


ዳዊትም ሰሎሞንን እንዲህ አለ፦ “ልጄ ሆይ! እኔ ለአምላኬ ለጌታ ቤት እንድሠራ በልቤ አስቤ ነበር።


ንጉሡም ዳዊት ተነሥቶ በመቆም እንዲህ አለ፦ “ወንድሞቼና ሕዝቤ ሆይ! ስሙኝ፤ ለጌታ ለቃል ኪዳኑ ታቦትና ለአምላካችን እግር ማረፊያ የሚሆን የማረፍያ ቤት ለመሥራት እኔ በልቤ አስቤያለሁ፤ ለግንባታም የሚያስፈልገውን አዘጋጅቻለሁ፤


“ከተፈተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊና ከቀይ ግምጃ የተሠሩ ዐሥር መጋረጆች ያሉበትን ድንኳን ሥራ፤ ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ኪሩቤል በእነርሱ ላይ ይሁኑ።


ልጁንም ሰሎሞንን ጠርቶ ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ስም ቤት እንዲሠራ አዘዘው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች