1 ዜና መዋዕል 15:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)17 ሌዋውያኑም የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤ ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም17 ስለዚህ ሌዋውያኑ የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን ሾሙ፤ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፣ ከወንድሞቻቸው ከሜራሪ ዘሮች የቂሳን ልጅ ኤታንን ሾሙ፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም17-21 ከመዘምራን ጐሣ የነሐስ ጸናጽል የሚያንሿሹ የኢዮኤል ልጅ ሄማን፥ የእርሱ ዘመድ የሆነው የበራክያ ልጅ አሳፍ፥ እንዲሁም ከመራሪ ጐሣ የቁሳያ ልጅ ኤታን ተመረጡ፤ በከፍተኛ ድምፅ የሚደረደረውን በገና በመምታት የእነርሱ ረዳቶች እንዲሆኑም ዘካርያስ፥ ያዕዚኤል፥ ሸሚራሞት፥ ይሒኤል፥ ዑኒ፥ ኤሊአብ፥ ማዕሤያና በናያ ተመረጡ። በዝቅተኛ ድምፅ የሚደረደረውን በገና እንዲመቱ ማቲትያ፥ ኤሊፈሌ፥ ሚቅኔያ፥ ዐዛዝያ እንዲሁም ከቤተ መቅደስ ዘበኞች መካከል ዖቤድኤዶምና ዩዒኤል ተብለው የሚጠሩት ሰዎች ተመረጡ። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)17 ሌዋውያኑም የኢዩኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳንን ልጅ ኢታንን፥ ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)17 ሌዋውያኑም የኢዮኤልን ልጅ ኤማንን፥ ከወንድሞቹም የበራክያን ልጅ አሳፍን፥ ከወንድሞቻቸውም ከሜራሪ ልጆች የቂሳን ልጅ ኤታንን፥ ምዕራፉን ተመልከት |