Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




1 ዜና መዋዕል 10:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፊታቸው ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተወግተው ወደቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ፍልስጥኤማውያን መጥተው በእስራኤላውያን ላይ አደጋ ጣሉ፤ እስራኤላውያንም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ በዚያም ጦርነት በጊልቦዓ ተራራ ላይ ብዙ እስራኤላውያን ተገደሉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በዚ​ያም ወራት ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ተዋጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያን ፊት ሸሹ፥ ተወ​ግ​ተ​ውም በጌ​ላ​ቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ዜና መዋዕል 10:1
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በማግስቱም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው።


ዳዊት ሄዶ፥ ሳኦልን በጊልቦዓ በገደሉ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን ከሰቀሉአቸው ስፍራ ከቤት ሻን አደባባይ ከሰረቁት ከያቤሽ ገለዓድ ሰዎች የሳኦልንና የልጁን የዮናታንን አጥንት ወሰደ፥


እናንተ የጊልቦዓ ተራሮች ሆይ፤ በዚያ የኀያሉ ሰው ጋሻ ረክሶአልና፤ የሳኦል ጋሻ በዘይት መወልወሉ ቀርቶአልና፤ ጠልም ሆነ ዝናብ አይውረድባችሁ፤ የቁርባን እህል የሚያበቅሉም እርሻዎች አይኑራችሁ።


ወሬ ነጋሪው ወጣትም እንዲህ አለ፤ “ድንገት ወደ ጊልቦዓ ተራራ ወጥቼ ነበር፤ እዚያም ሳኦል ጦሩን ተመርኩዞ ሳለ፥ ሠረገሎችና ፈረሰኞች ተከትለው ደረሱበት፤


ፍልስጥኤማውያን ተሰብስበው በመምጣት በሹኔም ሲሰፍሩ፥ ሳኦል ደግሞ እስራኤላውያንን ሁሉ ሰብስቦ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ሰፈረ።


በዚያን ዘመን ፍልስጥኤማውያን፥ እስራኤልን ለመውጋት ሠራዊታቸውን ሰበሰቡ። አኪሽም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ አብራችሁኝ ለጦርነት መውጣት እንዳለባችሁ ትረዳኛለህ” አለው።


ለኤሴልም ስድስት ልጆች ነበሩት፤ስማቸውም ይህ ነበረ፤ ዓዝሪቃም፥ ቦክሩ፥ እስማኤል፥ ሸዓርያ፥ አብድዩ፥ ሐናን፤ እነዚህ የኤሴል ልጆች ነበሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች