Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማሕልየ መሓልይ 6:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ርግቤ መደ​ም​ደ​ሚ​ያ​ዬም አን​ዲት ናት፤ ለእ​ናቷ አን​ዲት ናት፥ ለወ​ለ​ደ​ቻ​ትም የተ​መ​ረ​ጠች ናት። ቈነ​ጃ​ጅ​ትም አይ​ተው አሞ​ገ​ሱ​አት፥ ንግ​ሥ​ታ​ትና ቁባ​ቶ​ችም አመ​ሰ​ገ​ኑ​አት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 እንከን የሌለባት ርግቤ ግን ልዩ ናት፤ እርሷ ለወለደቻት የተመረጠች፣ ለእናቷም አንዲት ናት፤ ቈነጃጅት አይተው “የተባረክሽ ነሽ” አሏት፤ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኗት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ርግቤ፥ የእኔ እንከን የለሽ አንዲት ናት፥ ለእናትዋ አንዲት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው ብፅዕት አሉአት፥ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኑአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 እኔ ግን የምወደው አንዲትዋን ብቻ ነው፤ እርስዋም ምንም እንከን የሌለባት እንደ ርግብ የተዋበች ናት፤ እርስዋ ለእናትዋ አንድ ናት፤ የወለደቻት እናትዋም ከሁሉ አብልጣ ታፈቅራታለች፤ ቈነጃጅትም እርስዋን እየተመለከቱ ያወድሱአታል፤ ነገሥታትና የንጉሥ ቊባቶች ያሞግሡአታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ርግቤ መደምደሚያዬም አንዲት ናት፥ ለእናትዋ አንዲት ናት ለወለደቻትም የተመረጠች ናት። ቈነጃጅትም አይተው አሞገሱአት፥ ንግሥታትና ቍባቶችም አመሰገኑአት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማሕልየ መሓልይ 6:9
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልያም፥ “እኔ ብፅ​ዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ኛ​ልና” አለች፤ ስሙ​ንም አሴር ብላ ጠራ​ችው።


ለእ​ር​ሱም ሰባት መቶ ሚስ​ቶ​ችና ሦስት መቶ ቁባ​ቶች ነበ​ሩት።


በማ​ለዳ መገ​ሥ​ገ​ሣ​ች​ሁም ከንቱ ነው። ለወ​ዳ​ጆቹ እን​ቅ​ል​ፍን በሰጠ ጊዜ፥ እና​ንተ የመ​ከ​ራን እን​ጀራ የም​ት​በሉ፥ ከተ​ቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​በት ተነሡ።


ከም​ድር ዳርቻ ጦር​ነ​ትን ይሽ​ራል፤ ቀስ​ትን ይሰ​ብ​ራል፥ ጋሻ​ንም ይቀ​ጠ​ቅ​ጣል፥ በእ​ሳ​ትም የጦር መሣ​ሪ​ያን ያቃ​ጥ​ላል።


ፊት​ህን አሳ​የኝ፥ ቃል​ህ​ንም አሰ​ማኝ፤ ቃልህ ያማረ፥ ፊት​ህም የተ​ዋበ ነውና።


እኔ ተኝቼ ነበር፥ ልቤ ግን ነቅታ ነበር፤ ልጅ ወን​ድሜ ቃል ደጅ እየ​መታ መጣ፥ እኅቴ፥ ወዳጄ፥ ርግቤ፥ መደ​ም​ደ​ሚ​ያዬ ሆይ፥ በራሴ ጠል፥ በቍ​ን​ዳ​ላ​ዬም የሌ​ሊት ነጠ​ብ​ጣብ ሞል​ቶ​በ​ታ​ልና ክፈ​ች​ልኝ።


በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ሆኜ አየ​ዋ​ለሁ፤ በኮ​ረ​ብ​ቶ​ችም ላይ ሆኜ እመ​ለ​ከ​ተ​ዋ​ለሁ፤ እነሆ፥ ብቻ​ውን የሚ​ቀ​መጥ ሕዝብ ነው፤ በአ​ሕ​ዛ​ብም መካ​ከል አይ​ቈ​ጠ​ርም።


የላ​ይ​ኛ​ዪቱ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ግን በነ​ፃ​ነት የም​ት​ኖር ናት፤ እር​ስ​ዋም እና​ታ​ችን ናት።


እስ​ራ​ኤል ሆይ ብፁዕ ነህ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዳነ ሕዝብ እንደ አንተ ማን​ነው? እርሱ ያጸ​ን​ሃል፤ ይረ​ዳ​ሃ​ልም፤ ትም​ክ​ሕ​ትህ በሰ​ይ​ፍህ ነው፤ ጠላ​ቶ​ችህ ውሸ​ታ​ሞች ናቸው፤ አን​ተም በአ​ን​ገ​ታ​ቸው ላይ ትጫ​ና​ለህ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች