Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ማርቆስ 14:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

36 “አባ አባት ሆይ! ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን፤” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

36 “አባ፣ አባት ሆይ፤ ሁሉ ነገር ይቻልሃልና ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

36 “አባ፤ አባት ሆይ፤ ሁሉ ነገር ይቻልሃልና ይህን ጽዋ ከእኔ አርቀው፤ ነገር ግን የእኔ ፈቃድ ሳይሆን የአንተ ፈቃድ ይሁን” አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

36 እንዲህም አለ፤ “አባት ሆይ፥ ሁሉ ነገር ይቻልሃል፤ ይህን የመከራ ጽዋ ከእኔ አርቅልኝ፤ ነገር ግን እንደ አንተ ፈቃድ እንጂ እንደ እኔ ፈቃድ አይሁን።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

36 አባ አባት ሆይ፥ ሁሉ ይቻልሃል፤ ይህችን ጽዋ ከእኔ ውሰድ፤ ነገር ግን አንተ የምትወደው እንጂ እኔ የምወደው አይሁን አለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ማርቆስ 14:36
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልጆች እንደ መሆ​ና​ችሁ መጠን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አባ አባቴ ብላ​ችሁ የም​ት​ጠ​ሩ​ትን የል​ጁን መን​ፈስ በል​ባ​ችሁ አሳ​ደረ።


እኔ ከራሴ አን​ዳች አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ልም፤ እንደ ሰማሁ እፈ​ር​ዳ​ለሁ እንጂ፤ ፍር​ዴም እው​ነት ነው፤ የላ​ከ​ኝን ፈቃድ እንጂ የእ​ኔን ፈቃድ አል​ሻ​ምና።


ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።”


“አሁ​ንስ ነፍሴ ታወ​ከች፤ ግን ምን እላ​ለሁ? አባት ሆይ፥ ከዚች ሰዓት ነፍ​ሴን አድ​ናት፤ ነገር ግን ስለ​ዚህ ነገር ለዚች ሰዓት ደር​ሻ​ለሁ።


እንደ ሰውም ሆኖ ራሱን አዋ​ረደ፤ ለሞት እስከ መድ​ረ​ስም ታዘዘ፤ ሞቱም በመ​ስ​ቀል የሆ​ነው ነው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም ጴጥ​ሮ​ስን፥ “ሾተ​ል​ህን ወደ አፎቷ መልስ፤ አብ የሰ​ጠ​ኝን ጽዋ ሳል​ጠጣ እተ​ወ​ዋ​ለ​ሁን?” አለው።


ኢየሱስም ተመለከታቸውና “ይህ በእግዚአብሔር ዘንድ እንጂ በሰው ዘንድ አይቻልም፤ በእግዚአብሔር ዘንድ ሁሉ ይቻላልና፤” አለ።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “የእ​ኔስ መብል የላ​ከ​ኝን የአ​ባ​ቴን ፈቃድ አደ​ርግ ዘንድ፥ ሥራ​ው​ንም እፈ​ጽም ዘንድ ነው።


ጥቂትም ወደ ፊት እልፍ ብሎ በፊቱ ወደቀና ሲጸልይ “አባቴ! ቢቻልስ፥ ይህች ጽዋ ከእኔ ትለፍ፤ ነገር ግን አንተ እንደምትወድ ይሁን እንጂ እኔ እንደምወድ አይሁን፤” አለ።


እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ ‘በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ!


“እነሆ እኔ የሥጋ ለባሽ ሁሉ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ በውኑ ከእኔ የሚ​ሰ​ወር ነገር አለን?


የበ​ደ​ልን ነገር በእኔ አወጡ። የተኛ ሰው ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ አይ​ነ​ቃ​ምን?


በውኑ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ሳ​ነው ነገር አለን? የዛሬ ዓመት እንደ ዛሬው ጊዜ ወደ አንተ እመ​ለ​ሳ​ለሁ፤ ሣራም ልጅን ታገ​ኛ​ለች።”


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ሐሰት ሊሆን አይ​ቻ​ልም፤ በእ​ርሱ ለተ​ማ​ፀን ተጠ​ብ​ቆ​ልን ባለ ተስ​ፋ​ች​ንም ማመ​ንን ላጸ​ናን ለእኛ ታላቅ ደስታ አለን።


ደግሞ ሁለተኛ ሄዶ ጸለየና “አባቴ! ይህች ጽዋ ሳልጠጣት ታልፍ ዘንድ የማይቻል እንደ ሆነ፥ ፈቃድህ ትሁን፤” አለ።


መጣም፤ ተኝተውም አገኛቸው፤ ጴጥሮስንም “ስምዖን ሆይ! ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት ስንኳ ልትተጋ አልቻልህምን?


እነርሱም “እንችላለን፤” አሉት። ኢየሱስም “እኔ የምጠጣውን ጽዋ ትጠጣላችሁ፤ እኔ የምጠመቀውንም ጥምቀት ትጠመቃላችሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች