Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዮሐንስ 3:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ሥራው ክፉ የሆነ ሁሉ ብር​ሃ​ንን ይጠ​ላ​ልና፤ ክፉም ስለ​ሆነ ሥራው እን​ዳ​ይ​ገ​ለ​ጥ​በት ወደ ብር​ሃን አይ​መ​ጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ አድራጎቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፤ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ክፉ ነገር የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤ ክፉ ሥራውም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዮሐንስ 3:20
18 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዓለም እና​ን​ተን ሊጠ​ላ​ችሁ አይ​ች​ልም፤ እኔን ግን ይጠ​ላ​ኛል፤ ሥራዉ ክፉ እንደ ሆነ እኔ እመ​ሰ​ክ​ር​በ​ታ​ለ​ሁና።


የጻድቃን መንገዶች ግን እንደ ብርሃን ይበራሉ። ሙሉ ቀን እስኪሆንም ድረስ እየጨመሩ ይበራሉ።


ዕውቀትን ጠልተዋልና፥ እግዚአብሔርንም መፍራትን አልመረጡምና።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሥ​ዋ​ዕት የዋህ መን​ፈስ ነው፥ የተ​ዋ​ረ​ደ​ው​ንና የዋ​ሁን ልብ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ን​ቅም።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥን፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የም​ን​ጠ​ይ​ቅ​በት የይ​ምላ ልጅ ሚክ​ያስ የሚ​ባል አንድ ሰው አለ፤ ነገር ግን ክፉ እንጂ መል​ካም አይ​ና​ገ​ር​ል​ኝ​ምና እጠ​ላ​ዋ​ለሁ” አለው። የይ​ሁዳ ንጉሥ ኢዮ​ሣ​ፍ​ጥም፥ “ንጉሥ እን​ዲህ አይ​በል” አለ።


አላዋቂ ሰው የሚዘልፈውን አይወድድም፥ ከጠቢባንም ጋር አይነጋገርም።


እንዲህም ትላለህ፦ “እንዴት ትምህርትን ጠላሁ! ልቤም ከተግሣጽ እንዴት ራቀ!


ከሕግ ዐዋ​ቂ​ዎ​ችም አንዱ መልሶ፥ “መም​ህር ሆይ፥ ይህን ስትል እኛን እኮ መስ​ደ​ብህ ነው” አለው።


እነርሱ በጨለማ መንገድ ይሄዱ ዘንድ የቀናውን ጎዳና ለሚተዉ፥


አራ​ጣ​ንም በአ​ራጣ ላይ ይቀ​በ​ላሉ፤ ተን​ኰ​ልን በተ​ን​ኰል ላይ ይሠ​ራሉ፤ “እኔ​ንም ያው​ቁኝ ዘንድ እንቢ ብለ​ዋል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እው​ነ​ትን የሚ​ሠራ ግን ሥራው ይገ​ለጥ ዘንድ ወደ ብር​ሃን ይመ​ጣል፤ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብሎ ይሠ​ራ​ልና።


ምጣ​ዱ​ንም ወስዳ በፊቱ ገለ​በ​ጠች፤ እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አም​ኖ​ንም፥ “ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስ​ወጡ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ከእ​ርሱ ዘንድ ወጣ።


እር​ስ​ዋም በእ​ኩለ ሌሊት ተነ​ሥታ፥ እኔ አገ​ል​ጋ​ይህ ተኝቼ ሳለሁ፥ ልጄን ከብ​ብቴ ወሰ​ደች፤ በብ​ብ​ቷም አስ​ተ​ኛ​ችው፤ የሞ​ተ​ው​ንም ልጅ​ዋን በእኔ ብብት አስ​ተ​ኛ​ችው።


በዐይኑ ትኩር ብሎ የሚመለከት፥ ጠማማ ዐሳብን ያስባል፤ በከንፈሩም ክፉውን ሁሉ የሚያደርግ የክፋት ምድጃ ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች