Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ዜና መዋዕል 32:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 አሁ​ንም ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ስ​ታ​ችሁ፤ በእ​ነ​ዚ​ህም ቃላት እን​ድ​ት​ተ​ማ​መኑ አያ​ድ​ር​ጋ​ችሁ፤ አት​መ​ኑ​ትም፤ ከአ​ሕ​ዛ​ብና ከመ​ን​ግ​ሥ​ታት አማ​ል​ክት ሁሉ ሕዝ​ቡን ከእ​ጄና ከአ​ባ​ቶች እጅ ያድን ዘንድ ማንም አል​ቻ​ለም፤ ስለ​ዚ​ህም አም​ላ​ካ​ችሁ ከእጄ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ አይ​ች​ልም።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 አሁንም ሕዝቅያስ አያታልላችሁ፤ አያስታችሁም። የየትኛውም አገር ሕዝብ ወይም መንግሥት አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ወይም ከአባቶቼ እጅ መታደግ የቻለ ስለሌለ አትመኑት። የእናንተ አምላክማ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ ምንኛ ያንስ!”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፥ እንዲህም አያባብላችሁ፥ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ለማዳን ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ሊያድናቸሁ እንዴት ይችላል?’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህ ሕዝቅያስ በዚህ መንገድ አያታላችሁ! ወደ ስሕተትም አይምራችሁ! ከቶ እርሱን አትመኑ! የማንም ሕዝብ አምላክ የራሱን ሕዝብ ከማንኛውም የአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ ሊያድን የቻለበት ጊዜ የለም፤ ይህም የእናንተ አምላክ እናንተን ሊያድን እንደማይችል የተረጋገጠ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፤ እንዲህም አያባብላችሁ፤ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግስታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ያድን ዘንድ ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ እንዴት ይችላል?’”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ዜና መዋዕል 32:15
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ፈር​ዖ​ንም፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እለ​ቅቅ ዘንድ ቃሉን የም​ሰ​ማው እርሱ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማን ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አላ​ው​ቅም፤ እስ​ራ​ኤ​ል​ንም ደግሞ አል​ለ​ቅ​ቅም” አለ።


ሕዝ​ቅ​ያ​ስም፦ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያድ​ነ​ናል ብሎ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ። በውኑ የአ​ሕ​ዛብ አማ​ል​ክት ሀገ​ሮ​ቻ​ቸ​ውን ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ አድ​ነ​ዋ​ቸ​ዋ​ልን?


አሁ​ንስ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያይ​ደለ ለሰው ብዬ አስ​ተ​ም​ራ​ለ​ሁን? ወይስ ሰውን ደስ አሰ​ኛ​ለ​ሁን? ሰውን ደስ ላሰኝ ብወ​ድስ የክ​ር​ስ​ቶስ ባሪያ አይ​ደ​ለ​ሁም።


አሁን ግን እን​ደ​ም​ታ​ዩ​ትና እን​ደ​ም​ት​ሰ​ሙት ይህ ጳው​ሎስ ኤፌ​ሶ​ንን ብቻ ሳይ​ሆን መላ​ውን እስ​ያን አሳተ፤ ብዙ ሕዝ​ብ​ንም መለሰ፤ በሰው እጅ የሚ​ሠ​ሩ​ት​ንም ሁሉ አማ​ል​ክት አይ​ደ​ሉም አላ​ቸው።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ሦር ንጉሥ እጅ ያድ​ነ​ናል እያለ ለራብ፥ ለጥ​ምና ለሞት አሳ​ልፎ ይሰ​ጣ​ችሁ ዘንድ የሚ​ያ​ሳ​ስ​ታ​ችሁ ሕዝ​ቅ​ያስ አይ​ደ​ለ​ምን?


“ለይ​ሁዳ ንጉሥ ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም በአ​ሦር ንጉሥ እጅ አት​ሰ​ጥም ብሎ የም​ት​ታ​መ​ን​በት አም​ላ​ክህ አያ​ታ​ል​ልህ።


ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ ከእጄ ያድ​ና​ችሁ ዘንድ አይ​ች​ል​ምና ሕዝ​ቅ​ያስ አያ​ታ​ል​ላ​ችሁ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ በምን ታስ​ተ​ዋ​ለህ? አለው፤ እር​ሱም ወጥቼ በነ​ቢ​ያቱ ሁሉ አፍ ሐሰ​ተኛ መን​ፈስ እሆ​ና​ለሁ አለ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ ማሳ​ሳ​ትስ ታሳ​ስ​ተ​ዋ​ለህ፤ ይሆ​ን​ል​ሃ​ልም፤ ውጣ፤ እን​ዲ​ሁም አድ​ርግ አለ።


ባሪ​ያ​ዎ​ቹም ደግሞ በአ​ም​ላክ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በባ​ሪ​ያው በሕ​ዝ​ቅ​ያስ ላይ ሌላ ብዙ ነገር ተና​ገሩ።


ፈር​ዖ​ንም አላ​ቸው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ና​ንተ ጋር ይሁን፤ እነሆ፥ እና​ን​ተን ስለቅ ልጆ​ቻ​ች​ሁ​ንም መል​ቀቅ አለ​ብ​ኝን? ክፉ ነገር እን​ደ​ሚ​ገ​ጥ​ማ​ችሁ ዕወቁ።


አንተ አፍ​ህን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ እንደ አደ​ረ​ግህ እኔ ሰም​ቼ​አ​ለሁ።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች