Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




መዝሙር 55:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 ጓደኛዬ ወዳጆቹን አጠቃቸው፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ባልንጀራዬ የምለው ሰው እጁን በወዳጆቹ ላይ ሰነዘረ፤ ቃል ኪዳኑንም አፈረሰ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 አይለወጡምና፥ እግዚአብሔርንም አልፈሩትምና ከጥንት ጀምሮ የነበረ እግዚአብሔር ሰምቶ ያጐሰቁላቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




መዝሙር 55:20
20 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በዚያን ዘመን ንጉሥ ሄሮድስ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ሰዎችን ማሳደድ ጀመረ፤


ከእርሱ ጋር የገባሁትን ቃል ኪዳን አላፈርስም፤ ለእርሱ ከሰጠሁትም የተስፋ ቃል አንዱን እንኳ አላስቀርም።


በመልካም ፈንታ ክፉ፥ በፍቅር ፈንታ ጥላቻ ይመልሱልኛል።


ለንጉሡ እታዘዛለሁ ብለህ በመሐላ ለእግዚአብሔር ቃል ስለ ገባህ ለንጉሥ ታማኝ ሁን።


አሁን ግን በመረጥከው ንጉሥ ላይ ተቈጥተሃል፤ ተለይተኸዋል፤ ጥለኸዋልም።


ለእርሱ ያለኝ ፍቅር ዘለዓለማዊ ነው፤ ከእርሱም ጋር የገባሁት ቃል ኪዳን ከቶ አይፈርስም።


ሰውየው ግን እንዲህ ሲል መለሰ፤ “አንድ ሺህ ጥሬ ብር እንኳ ብትሰጠኝ በንጉሡ ልጅ ላይ እጄን አላነሣም፤ ንጉሡ ለአንተ፥ ለአቢሳና ለኢታይ ‘ለእኔ ስትሉ በወጣቱ አቤሴሎም ላይ ለሞት የሚያደርስ ጒዳት እንዳታደርሱበት’ ሲል የሰጣችሁን ትእዛዝ ሁላችንም ሰምተናል፤


እንግዲህ የእስራኤል መሪዎች ሁሉ በኬብሮን ወደ ነበረው ወደ ዳዊት የመጡት በዚህ ዐይነት ነበር፤ እርሱም ከእነርሱ ጋር በእግዚአብሔር ፊት የቃል ኪዳን ስምምነት አደረገ፤ እነርሱም ቀብተው በእስራኤል ላይ አነገሡት።


ከዚህ በኋላ የይሁዳ ሰዎች ወደ ኬብሮን መጡ፤ ዳዊትንም ቀብተው የይሁዳ ንጉሥ አደረጉት። ዳዊት ገለዓዳውያን የሆኑ የያቤሽ ሰዎች ሳኦልን እንደ ቀበሩት በሰማ ጊዜ፥


ዛሬ በዚህ ሰዓት በዋሻው ውስጥ ሳለህ እግዚአብሔር በእጄ ጥሎህ እንደ ነበር አንተ ራስህ ማየት ትችላለህ፤ አንዳንድ ሰዎችም እንድገድልህ መክረውኝ ነበር፤ ነገር ግን አንተ ‘እግዚአብሔር የቀባህ ንጉሥ ነህና እኔ በጌታዬ ላይ እጄን አላነሣም’ ብዬ ራራሁልህ፤


ከዚህም በኋላ ሳኦል በአጠገቡ ወደቆሙት ዘብ ጠባቂዎች መለስ ብሎ “እነዚህን የእግዚአብሔርን ካህናት ግደሉ! እነርሱ ከዳዊት ጋር በእኔ ላይ ዐምፀውብኛል፤ እንዲሁም ሁሉን ነገር እያወቁ ዳዊት መኰብለሉን እንኳ አልነገሩኝም” አላቸው፤ ዘብ ጠባቂዎቹ ግን “የእግዚአብሔርን ካህናት አንገድልም” አሉ።


ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን አያመልኩም፤ ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶች፥ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም።


ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ በድንገትም ተዋርደው ወደ ኋላቸው ይሸሻሉ።


እግዚአብሔር ሆይ! ዙፋንህ ከጥንት ጀምሮ የጸና ነው፤ አንተም ከዘመናት ሁሉ በፊት አምላክ ነህ።


እግዚአብሔር ሆይ ዐይኖችህ እውነትን የሚመለከቱ አይደሉምን? አንተ ቀሠፍሃቸው፤ እነርሱ ግን ከምንም አልቈጠሩትም፤ አደቀቅሃቸው፤ እነርሱ ከስሕተታቸው መማር እምቢ አሉ፤ እልኸኝነትን አበዙ እንጂ፥ ከኃጢአታቸው መመለስ አልፈለጉም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች