Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ስለ ወይኑ ተክል ለውዴ የፍቅር ዘፈን ልዝፈን ውዴ እጅግ ለም በሆነ ኰረብታ ላይ የወይን ተክል ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ስለ ወዳጄ፣ ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ ወዳጄ በለምለም ኰረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ደግሞም ስለ ወይን ቦታው ልዘምር፤ ስለ ወዳጄ፤ ወዳጄ በለምለም ኮረብታ ላይ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 አሁን የወ​ይ​ኔን ቦታ በተ​መ​ለ​ከተ የወ​ዳ​ጄን መዝ​ሙር ለወ​ዳጄ እዘ​ም​ራ​ለሁ። ለወ​ዳጄ በፍ​ሬ​ያ​ማው ቦታ ላይ የወ​ይን ቦታ ነበ​ረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 አሁን ስለ ወዳጄና ስለ ወይን ቦታው ለወዳጄ ቅኔ እቀኛለሁ። ለወዳጄ በፍሬያማው ኮረብታ ላይ የወይን ቦታ ነበረው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 5:1
23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን በምሳሌ እንዲህ ሲል ይነግራቸው ጀመር፦ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ዙሪያውንም ዐጠረ፤ የወይን መጭመቂያ የሚሆን ጒድጓድ ቆፍሮ አበጀ፤ ለወይኑ ጥበቃ የሚያገለግል ከፍተኛ የግንብ ማማ ሠራ፤ ከዚህም በኋላ የአትክልቱን ቦታ ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሩቅ አገር ሄደ።


ቀጥሎም ኢየሱስ ይህን ምሳሌ ለሕዝቡ መናገር ጀመረ፦ “አንድ ሰው የወይን ተክል ተከለ፤ ለገበሬዎች አከራየውና ወደ ሌላ አገር ሄደ፤ ሳይመለስም ብዙ ጊዜ ቈየ።


“እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ፤ አትክልተኛውም አባቴ ነው፤


ደግሞም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “ሌላም ምሳሌ ስሙ፤ የወይን አትክልት የተከለ አንድ ሰው ነበረ፤ እርሱ በወይኑ አትክልት ዙሪያ አጥር ዐጠረ፤ የወይን መጭመቂያ የሚሆን ጒድጓድ ቆፍሮ አበጀ፤ ለወይኑ ጥበቃ የሚያገለግል ረዥም ግንብ ሠራ፤ ከዚህ በኋላ የአትክልቱን ቦታ ለገበሬዎች አከራይቶ ወደ ሌላ አገር ሄደ።


እኔ ከተመረጠ ዘር መልካም የወይን ተክል አድርጌ ተክዬሽ ነበር፤ አንቺ ግን ተለውጠሽ እንደ ተበላሸ የበረሓ የወይን ተክል ሆነሻል።


የወይን ሐረግን ከግብጽ አመጣህ፤ ሌሎች ሕዝቦችን አስወግደህ በምድራቸው እርስዋን ተከልክ።


ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በአሸንድዬ አበባዎች መካከል መንጋውን ያሰማራል።


ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፤ በሱፍ አበባዎች መካከል መንጋውን ያሰማራል።


አፉ እንደ ማር. የጣፈጠ ነው፤ ሁለንተናውም የደስ ደስ አለው፤ እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት እንግዲህ ውዴና ወዳጄ ይህን የመሰለ ነው።


እኔ ተኝቼአለሁ፤ ልቤ ግን ነቅቶአል፤ ውዴ እንዲህ እያለ በር ሲያንኳኳ ሰማሁት፤ “ውድ እኅቴ የሆንሽ ሙሽራዬ ሆይ! እንከን የሌለብሽ ርግቤ ሆይ! እባክሽ በሩን ክፈችልኝ፤ ራሴ በጠል ርሶአል ጠጒሬም በሌሊት ካፊያ ረስርሶአል።”


ልቤ መልካም ርእስን ያፈልቃል፤ ጽሑፌም የሚያተኲረው በንጉሡ ላይ ነው፤ አንደበቴም እንደ መልካም ጸሐፊ ብዕር ነው።


እግዚአብሔር ሆይ! ስለ ታማኝነትህና ስለ ትክክለኛ ፍርድህ እዘምራለሁ፤ አዜማለሁም።


የምትወደው ሕዝብህ ከጒዳት እንዲድን በኀይልህ ታደገን፤ ጸሎታችንን ስማ።


ብዙ መሪዎች የወይን ተክል ቦታዬን አጥፍተዋል፤ የእርሻ ቦታዎቼንም ረጋግጠዋል፤ ደስ የምታሰኘውን ምድሬንም ወደ በረሓነት ለውጠዋታል።


“የሰው ልጅ ሆይ! የወይን ግንድ ከሌሎች ዛፎች ግንድ ቅርንጫፎች ከዱር ዛፎች ቅርንጫፍ በምን ይበልጣል?


የእስራኤል ሕዝብ ብዙ ዘለላ እንደ ያዘ የወይን ተክል ናቸው፤ ፍሬ በበዛላቸው መጠን ብዙ የጣዖት መሠዊያዎችን ሠሩ፤ ምድራቸው ፍሬያማ ሆና በበለጸገችላቸው መጠን የጣዖት መስገጃ ዐምዶችን አስጊጠው ሠሩ።


እነሆ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ወደ መልካሚቱ ለምለም ምድር ሊያስገባህ አምጥቶሃል፤ ያቺም ምድር ከሸለቆዎችና ከኮረብቶች የሚመነጩ ወንዞችና ጅረቶች፥ ፈሳሾች ምንጮችም ይገኙበታል፤


በልተህ ትጠግባለህ፤ ይህችን ለም ምድር የሰጠህን እግዚአብሔር አምላክህንም ታመሰግናለህ።


እናትህ በውሃ አጠገብ እንደ ተተከለች የወይን ተክል ነበረች፤ እርስዋም ከውሃው መትረፍረፍ የተነሣ በቅርንጫፎችዋና በፍሬ እንደ ተሞላች የወይን ተክል ሆነች፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች