Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሕዝቅኤል 41:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ቀጥሎም የቤተ መቅደሱ ማእከል ወደ ሆነው የተቀደሰ ስፍራ አስገባኝ፤ ወደ እርሱ የሚወስደውንም መተላለፊያ ሲለካ የሁለቱ ጐን ትይዩ ርዝመት ስድስት ክንድ ሆነ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ከዚያም ወደ መቅደሱ አገባኝ፤ ዐምዶቹንም ለካ፤ የዐምዶቹም ወርድ በአንዱ በኩል ስድስት ክንድ፣ በሌላውም በኩል ስድስት ክንድ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ወደ መቅደሱም አገባኝ፥ የድንኳኑን አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድስት ክንድ በዚያም ወገን ስድስት ክንድ አድርጎ ለካ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ወደ መቅ​ደ​ሱም አገ​ባኝ፤ የግ​ን​ቡ​ንም አዕ​ማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድ​ስት ክንድ፥ በዚ​ያም ወገን ስድ​ስት ክንድ አድ​ርጎ ለካ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ወደ መቅደሱም አገባኝ፥ የግንቡንም አዕማድ ወርድ በዚህ ወገን ስድስት ክንድ በዚያም ወገን ስድስት ክንድ አድርጎ ለካ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሕዝቅኤል 41:1
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የተቀደሰው ቦታና ቅድስተ ቅዱሳኑ ድርብ መዝጊያዎች አሉአቸው።


ከዚያ በኋላ ሰውዬው ወደ ውጪው አደባባይ አመጣኝ፤ በአደባባዩ ዙሪያ የድንጋይ ንጣፍና ክፍሎች ነበሩ ከንጣፉም ፊት ለፊት ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።


የተናገረኝም መልአክ ከተማይቱንና ደጃፎችዋን፥ የግንቡንም አጥር የሚለካበት የወርቅ ዘንግ ነበረው፤


እንዲህም የሚል ከፍተኛ ድምፅ ከዙፋኑ ሲወጣ ሰማሁ፤ “እነሆ! የእግዚአብሔር ማደሪያ ከሰዎች ጋር ነው፤ ከእነርሱም ጋር ይኖራል፤ እነርሱም የእርሱ ሕዝብ ይሆናሉ። እግዚአብሔር ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤


ድል የሚነሣውን በአምላኬ ቤተ መቅደስ ዐምድ አደርገዋለሁ፤ ከዚያም ከቶ አይወጣም፤ የአምላኬን ስምና የአምላኬን ከተማ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ፤ ይህችም ከተማ ከሰማይ ከአምላኬ ዘንድ የምትወርደው አዲሲቱ ኢየሩሳሌም ናት፤ የእኔንም አዲስ ስም በእርሱ ላይ እጽፋለሁ።


ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።


የመቅደሱም የበር መቃኖች ቅርጽ ሁሉ እኩልነት ያለው አራት ማእዘን ነበር።


ከዚያም አልፎ ወደ ውስጠኛው ክፍል ገባ፤ ወደ እርሱ የሚያስገባውንም መተላለፊያ ሲለካው ርዝመቱ ሁለት ክንድ ወርዱ ስድስት ክንድ ሆነ፤ በግራና ቀኝ የሚገኙትም ግንቦች የእያንዳንዱ ውፍረት ሰባት ክንድ ሆነ።


ቤተ መቅደሱ በውስጥ በኩል ርዝመቱ ኻያ ሰባት ሜትር፥ ወርዱ ዘጠኝ ሜትር፥ ቁመቱ ዐሥራ ሦስት ሜትር ተኩል ነበር፤


ከዚህም በኋላ ያ ሰው በውጭ በኩል ወደሚገኘው አደባባይ ወሰደኝ፤ ከባዶ ቦታ ፊት ለፊት እና በሰሜን በኩል ካለው ሕንጻ ትይዩ ወደነበሩት ክፍሎች አመጣኝ።


የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር ከወጡ ከአራት መቶ ሰማኒያ ዓመት በኋላ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ ተብሎ በሚጠራው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች