Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 19:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

32 “በአዛውንት ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

32 “ ‘ዕድሜው ለገፋ ተነሥለት፤ ሽማግሌውን አክብር፤ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

32 “በዕድሜ የገፉ ሽማግሌዎች ሲመጡ ስታይ ከተቀመጥክበት በመነሣት አክብራቸው፤ እኔን አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

32 “በሽ​በ​ታሙ ፊት ተነሣ፤ ሽማ​ግ​ሌ​ው​ንም አክ​ብር፤ አም​ላ​ክ​ህን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ፍራ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

32 በሽበታሙ ፊት ተነሣ፥ ሽማግሌውንም አክብር፥ አምላክህንም ፍራ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 19:32
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እርሷም አባትዋን፥ “ፊትህ ለመቆም ስላልቻልሁ አትቆጣብኝ፥ በሴቶች የሚደርስ ግዳጅ ደርሶብኛልና” አለችው። እርሱም ፈለገ፥ ነገር ግን ተራፊምን አላገኘም።


ዮሴፍም ከጉልበቱ ፈቀቅ አደረጋቸው፥ ወደ ምድርም በግምባሩ ሰገደ።


ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤


በታላቅ ኃይልና በሥልጣን ከግብጽ ምድር ላወጣኋችሁ ለእኔ ለእግዚአብሔር ታዛዦች ሁኑ፤ መስገድና መሥዋዕት ማቅረብ የሚገባችሁ ለእኔ ብቻ ነው፤


ከእርሱ ይልቅ ሽማግሌዎች ነበሩና ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር የሚናገርበትን ጊዜ ይጠባበቅ ነበር።


የቡዛዊውም የባርክኤል ልጅ ኤሊሁ ተናገረ፤ እንዲህም አለ፦ “እኔ በዕድሜ ታናሽ ነኝ፥ እናንተ ግን ሽማግሌዎች ናችሁ፥ ስለዚህም ሰጋሁ፥ የማውቀውን እገልጥላችሁ ዘንድ ፈራሁ።


የሸበተ ጠጉር የክብር ዘውድ ነው፥ እርሱም በጽድቅ መንገድ ይገኛል።


የጎበዛዝት ክብር ጉልበታቸው ናት፥ የሽማግሌዎችም ጌጥ ሽበት ነው።


የወለደህን አባትህን ስማ፥ እናትህም ባረጀች ጊዜ አትናቃት።


ሕዝብ እርስ በርሱ ይጨቋቈናል፤ ሰው በሰው ላይ፤ ባልንጀራ በባልንጀራው ላይ፤ ወጣቱ በሽማግሌው ላይ፤ ተራው ሰው በተከበረው ላይ ይነሣል።


አለቆች በእጃቸው ተሰቀሉ፥ የሽማግሌዎች ፊት አልታፈረም።


መስማት የተሳነውን አትስደብ፥ በዓይነ ስውሩም ፊት ዕንቅፋት አታኑር፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ለሁሉ የሚገባውን ስጡ፤ ግብር ለሚገባው ግብርን፥ ቀረጥ ለሚገባው ቀረጥን፥ መፈራት ለሚገባው መፈራትን፥ ክብር ለሚገባው ክብርን ስጡ።


ሽማግሌን እንደ አባት አድርገህ ምከር እንጂ አትገሥጽ፤ እንዲሁም ጎልማሶችን እንደ ወንድሞች፥


ሰውን ሁሉ አክብሩ፤ ወንድሞችን ውደዱ፤ እግዚአብሔርን ፍሩ፤ ንጉሥን አክብሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች