የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽሐፈ ሲራክ 33 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 33

ስለ እስ​ራ​ኤል ድኅ​ነት የቀ​ረበ ጸሎት

1 የኀ​ይል ሁሉ ፈጣሪ አቤቱ፥ ይቅር በለን፤ ተመ​ለ​ስ​ል​ንም።

2 በአ​ሕ​ዛብ ሁሉ ላይ አን​ተን መፍ​ራ​ትን አሳ​ድር።

3 ልዩ በሆኑ ወገ​ኖ​ችም ላይ እጅ​ህን አንሣ፤ ኀይ​ል​ህ​ንም ይዩ።

4 እነ​ርሱ እያዩ በእኛ ዘንድ እንደ ተመ​ሰ​ገ​ንህ፥ እን​ደ​ዚሁ እኛ እያ​የን በእ​ነ​ርሱ ዘንድ ተመ​ስ​ገን።

5 አቤቱ ያለ​አ​ንተ ሌላ ፈጣሪ የለ​ምና፥ እኛ እን​ዳ​ወ​ቅ​ንህ እነ​ር​ሱም ይወ​ቁህ።

6 ተአ​ም​ራ​ት​ህን አሳይ፤ ጌት​ነ​ት​ህ​ንም ግለጥ።

7 በእ​ጅህ ኀይል በቀ​ኝ​ህም ክብር፥

8 ጥፋ​ትን አም​ጣ​ባ​ቸው፤ መቅ​ሠ​ፍ​ት​ንም ላክ​ባ​ቸው።

9 ዐመ​ፀ​ኛ​ው​ንም አጥ​ፋው፤ ጠላ​ት​ንም ቀጥ​ቅ​ጠው።

10 ድንቅ ሥራ​ህን ይነ​ግሩ ዘንድ የባ​ሮ​ች​ህን መሐላ አስብ፤ የሚ​ጠ​ፉ​ባ​ት​ንም ቀን ፈጥ​ነህ አድ​ር​ጋት።

11 በቍ​ጣና በእ​ሳት ቅሠ​ፋ​ቸው፤ ከእ​ነ​ር​ሱም ያመ​ለ​ጡ​ትን አጥ​ፋ​ቸው፤ በወ​ገ​ኖ​ች​ህም ላይ ክፉ ያደ​ረጉ ሰዎ​ችን ሞት ያግ​ኛ​ቸው።

12 ያለ እኛ ሌላ ሰው የለም የሚሉ የጠ​ላ​ቶ​ችን አለ​ቆች ራስ ስበር።

13 የያ​ዕ​ቆ​ብን ልጆች ሁሉ ሰብ​ስ​ባ​ቸው።