የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽሐፈ ሲራክ 30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 30

ስለ ልጆች

1 ልጁን የሚ​ወድ ሰው በፍ​ጻ​ሜው በእ​ርሱ ደስ ይለው ዘንድ፥ ልጁን መቅ​ጣ​ትን ቸል አይ​ልም።

2 ልጁን የሚ​ቀጣ ሰው በእ​ርሱ ደስ ይለ​ዋል፤ በወ​ዳ​ጆ​ቹም ዘንድ ይመ​ካ​በ​ታል።

3 ልጁን ያስ​ተ​ማረ ሰው ጠላ​ቱን ያስ​ቀ​ናል፥ በወ​ዳ​ጆ​ቹም ዘንድ በእ​ርሱ ደስ ይለ​ዋል።

4 ከእ​ርሱ በኋላ እንደ እርሱ ያለ ልጅ ተክ​ት​ዋ​ልና አባቱ ቢሞ​ትም እን​ዳ​ል​ሞተ ይሆ​ናል።

5 በሕ​ይ​ወ​ቱም ሳለ በልጁ ደስ ይለ​ዋል፤ ቢሞ​ትም ልቡ አያ​ዝ​ንም።

6 ከእ​ርሱ በኋላ ጠላ​ቶ​ቹን የሚ​በ​ቀል፥ ለወ​ዳ​ጆ​ቹም ዋጋን የሚ​ከ​ፍል ልጅ ተክ​ት​ዋ​ልና።

7 ልጆ​ቹን የሚ​ያ​ባ​ልግ ሰው​ነቱ ይቈ​ስ​ላል፤ በጩ​ኸ​ታ​ቸ​ውም ጊዜ ልቡ በሕ​መም ይሠ​ቃ​ያል።

8 ያል​ተ​ገራ ፈረስ ገር​ጋሪ ይሆ​ናል፤ ያል​ተ​ቀጣ ልጅም አው​ታታ ይሆ​ናል፤

9 ልጅ​ህን ካቀ​ማ​ጠ​ል​ኸው ይበ​ረ​ታ​ታ​ብህ ዘንድ ይመ​ለ​ሳል፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ብት​ጫ​ወት ያሳ​ዝ​ንህ ዘንድ ይመ​ለ​ሳል።

10 እን​ዳ​ያ​ሳ​ዝ​ን​ህም አት​ሳ​ቅ​ለት፤ በፍ​ጻ​ሜም ጥር​ስ​ህን ያረ​ግ​ፍ​ሃል።

11 በወ​ጣ​ት​ነቱ ጊዜ ልጅ​ህን ስድ አት​ል​ቀ​ቀው። በስ​ሕ​ተ​ቱም ጊዜ ቸል አት​በ​ለው፤

12 በአ​ደገ ጊዜ እን​ዳ​ያ​ም​ፅ​ብህ በል​ጅ​ነቱ ጊዜ ጎኑን ግረ​ፈው።

13 በእ​ርሱ ጥፋት እን​ዳ​ታ​ፍር ልጅ​ህን ቅጣው፤ ያገ​ለ​ግ​ል​ሃ​ልም።

ስለ ጤን​ነት

14 ሰው​ነቱ ከታ​መ​መና ሆዱ ከታ​ሰረ ባለ​ጸጋ፥ ሰው​ነቱ ጤነኛ የሆ​ነና ሆዱ የተ​ከ​ፈተ ድሃ ይሻ​ላል።

15 ሰው​ነ​ትህ ጤነኛ ይሁን፤ ሆድ​ህም የተ​ከ​ፈተ ይሁን፤ ይህም ከባ​ለ​ጸ​ግ​ነት ሁሉ ይሻ​ላል። ከባ​ለ​ጸ​ግ​ነ​ትና ከገ​ን​ዘ​ብም ሁሉ የሰ​ው​ነት ጤን​ነት ይሻ​ላል።

16 በጤና ከመ​ኖር ባለ​ጸ​ግ​ነት አይ​መ​ረ​ጥም፤ ከልብ ደስ​ታም የሚ​ሻል ደስታ የለም።

17 ከመ​ረረ ኑሮና ከቍ​ር​ጥ​ማት በሽታ ሞት ይሻ​ላል።

18 በተ​ዘጋ አፍ የሚ​ቀ​ርብ መብል ወደ መቃ​ብር እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ እህል ነው።

19 ለጣ​ዖ​ታት መሠ​ዋት ምን ይጠ​ቅ​ማል? እነ​ርሱ አይ​በ​ሉ​ምና፥ እነ​ር​ሱም አይ​ጠ​ጡ​ምና፥ እነ​ር​ሱም አያ​ሸ​ት​ቱ​ምና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ሠ​ፈ​ውም ሰው እን​ደ​ዚሁ ነው።

20 ጃን​ደ​ረባ ቆን​ጆ​ዪ​ቱን ባቀ​ፋት ጊዜ እን​ደ​ሚ​ያ​ዝን፥ በዐ​ይ​ኖቹ እያየ ያዝ​ናል።

21 ነፍ​ስ​ህን አታ​ሳ​ዝን፤ ልብ​ህ​ንም አታ​ስ​ጨ​ንቅ።

22 የል​ቡና ደስታ ለሰው ሕይ​ወቱ ነው፤ የሰ​ው​ነት ደስ​ታም ዘመ​ንን ያረ​ዝ​ማል።

23 ኀዘ​ንን ከአ​ንተ ታር​ቃት ዘንድ ልብ​ህን አጽ​ና​ናት፤ ሰው​ነ​ት​ህ​ንም አረ​ጋ​ጋት፤ ኀዘን ብዙ ሰዎ​ችን አጥ​ፍ​ታ​ቸ​ዋ​ለ​ችና፤ ኀዘ​ንም የም​ት​ጠ​ቅ​መው የለ​ምና።

24 ቅና​ትና ቍጣ የሕ​ይ​ወት ዘመ​ንን ያሳ​ን​ሳሉ፤ ኀዘ​ንም ጊዜው ሳይ​ደ​ርስ ያስ​ረ​ጃል።

25 አጫ​ጅን እየ​ተ​ከ​ተለ እን​ደ​ሚ​ቃ​ርም ሰው፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በረ​ከት ደረ​ስሁ። እንደ ወይን ለቃ​ሚም መጭ​መ​ቂ​ያ​ዬን ሞላሁ።

26 ጠቢ​ባን ይሆኑ ዘንድ ለሚ​ወዱ ሰዎ​ችም ሁሉ ነው እንጂ፥ የደ​ከ​ምኩ ለእኔ ብቻ እን​ዳ​ይ​ደለ እነሆ አስ​ተ​ውሉ።

27 የሕ​ዝቡ መኳ​ን​ንት ስሙኝ፥ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች አድ​ም​ጡኝ።

28 ልጅ​ህ​ንና ሚስ​ት​ህን፥ ወን​ድ​ም​ህ​ንና ወዳ​ጅ​ህን አንተ በሕ​ይ​ወት ሳለህ፥ በገ​ን​ዘ​ብህ ላይ አታ​ሠ​ል​ጥ​ና​ቸው ኋላ እን​ዳ​ት​ጸ​ጸት፥ ትለ​ም​ና​ቸ​ውም ዘንድ እን​ዳ​ት​መ​ለስ፥ በቤ​ትህ ባዕድ ሰው አት​ሹም።

29 አንተ በሕ​ይ​ወት ሳለህ፥ ትን​ፋ​ሽ​ህም ሳለች ግብ​ር​ህን አት​ለ​ውጥ።

30 አንተ የል​ጆ​ች​ህን እጅ ደጅ ከም​ት​ጠና፤ ልጆ​ችህ አን​ተን ቢለ​ም​ኑህ ይሻ​ል​ሃል።

31 በም​ት​ሠ​ራው ሥራ ሁሉ ብልህ ሁን፤ በተ​ሾ​ም​ህ​በ​ትም ሁሉ ራስ​ህን አታ​ስ​ነ​ቅፍ።

32 የሕ​ይ​ወት ዘመ​ንህ ሁሉ በአ​ለቀ ጊዜ፤ ፍጻ​ሜ​ህም በደ​ረሰ ጊዜ፥ ያን ጊዜ ገን​ዘ​ብ​ህን አው​ርስ።

33 አህ​ያ​ህን ገለባ አብ​ላው፤ ጫነው፤ በአ​ለ​ን​ጋም ግረ​ፈው፤ አገ​ል​ጋ​ይ​ህ​ንም ቅጣው፤ መግ​በው፤ ግዛ​ውም።

34 አገ​ል​ጋ​ዮ​ች​ህ​ንም እን​ዲ​ሠሩ አድ​ር​ጋ​ቸው፤ ዕረ​ፍ​ት​ንም ታገ​ኛ​ለህ፤ ብታ​ቦ​ዝ​ና​ቸው ግን ይከ​ራ​ከ​ሩህ ዘንድ፥ ከአ​ን​ተም ነጻ ይወጡ ዘንድ ይወ​ድ​ዳሉ።

35 ቀን​በር መጫን አን​ገ​ትን ዝቅ ያደ​ር​ገ​ዋል፤ አለ​ን​ጋና እግር ብረ​ትም ለክፉ አገ​ል​ጋይ ነው።

36 አገ​ል​ጋ​ይ​ህን እን​ዲ​ሠራ አድ​ር​ገው፥ አቦ​ዝ​ነህ አታ​ኑ​ረው።

37 ቦዘ​ኔ​ነት ብዙ ክፋ​ትን ታስ​ተ​ም​ራ​ለ​ችና።

38 የሚ​ች​ለ​ውን ያህል ሥራ​ውን ስጠው፤ ባይ​ታ​ዘዝ ግን እግር ብረ​ቱን አጽ​ና​በት፤ ነገር ግን ሥጋ​ዊ​ውን ሁሉ አት​መ​ነው። ያለ ምክ​ርም የም​ት​ሠ​ራው ሥራ አይ​ኑር፤

39 አገ​ል​ጋይ ቢኖ​ርህ እንደ ራስህ ይሁን፤ በዋጋ ገዝ​ተ​ኸ​ዋ​ልና፥ ደግ አገ​ል​ጋ​ይም ቢኖ​ርህ እንደ ወን​ድ​ምህ አድ​ር​ገው፤ እንደ ራስ​ህም ውደ​ደው።

40 ክፉ ነገር ብታ​ደ​ር​ግ​በት ግን ይኰ​በ​ል​ል​ብ​ሃል፤ ያመ​ል​ጥ​ሃ​ልም፤ ከዚህ በኋላ በየት ጎዳና ታገ​ኘ​ዋ​ለህ?