የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽሐፈ ሲራክ 28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 28

1 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለሚ​ታ​ገሥ ሰው ይበ​ቀ​ል​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱ​ንም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።

2 ባል​ን​ጀ​ራህ የበ​ደ​ለ​ህን በደል ይቅር በለው፥ የዚ​ያን ጊዜ ንስሓ ከገ​ባህ ኀጢ​አ​ት​ህን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ል​ሃል።

3 አንተ ሰው ስት​ሆን እንደ አንተ ያለ​ውን ሰው ከተ​ቀ​የ​ምህ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እን​ዴት ይቅር በለኝ ትለ​ዋ​ለህ?

4 እንደ አንተ ያለ ሰውን ይቅር ሳትል፥ ኀጢ​አ​ት​ህን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ልህ ዘንድ እን​ግ​ዲህ እን​ዴት ትለ​ም​ነ​ዋ​ለህ?

5 ሥጋ ለባሹ ቂመኛ ከሆነ ኀጢ​አ​ቱን ማን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል?

6 ፍጻ​ሜ​ህን ዐስ​በህ ጠብን ተዋት። ሞት​ንና ሙስና መቃ​ብ​ርን ዐስብ፤ ትእ​ዛ​ዙ​ንም ጠብቅ።

7 ሕጉን ዐስ​በህ ባል​ን​ጀ​ራ​ህን አት​ቀ​የም፤ የል​ዑ​ልን ፍር​ዱን ዐስ​በህ ቍጣን አር​ቃት።

8 ኀጢ​አ​ቶ​ች​ህን ታሳ​ን​ስ​ልህ ዘንድ ክር​ክ​ርን ተዋት፤ ቍጡ ሰው ክር​ክ​ርን ያነ​ሣ​ሣል።

9 ኀጢ​አ​ተኛ ሰውም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ያደ​ክ​ማል፤ ወዳ​ጆ​ቹ​ንም ያጣ​ላል።

10 በእ​ን​ጨቱ ልክ የእ​ሳቱ ነዲድ ይበ​ዛል፤ በክ​ር​ክ​ሩም ብዛት መጠን ጠቡ ይበ​ዛል፤ የሰው ኀይሉ በቁ​መቱ መጠን ነው፤ በባ​ለ​ጸ​ግ​ነ​ቱም ብዛት መጠን ቍጣ​ውን ያበ​ዛ​ታል።

11 መታ​በ​ይን የሚ​ያ​በ​ዛት ሰው እሳ​ትን ያቀ​ጣ​ጥ​ላ​ታል፤ ለጠብ የሚ​ቸ​ኵል ሰውም ፈጥኖ ደምን ያፈ​ስ​ሳል።

ክፉ ምላስ

12 ፍምን እፍ ብት​ላት ትነ​ድ​ዳ​ለች፤ ትፍ ብት​ል​ባ​ትም ትጠ​ፋ​ለች፤ ሁለ​ቱም ከአ​ንድ አፍ ይወ​ጣሉ።

13 ሐሜ​ተ​ኛ​ንና ሁለት አን​ደ​በት ያለ​ውን ሰው ይረ​ግ​ሙ​ታል፤ ብዙ ወዳ​ጆ​ችን አጋ​ድ​ሎ​አ​ልና።

14 ነገረ ሠሪ አን​ደ​በት ብዙ ሰዎ​ችን አወ​ካ​ቸው፤ ከሕ​ዝ​ብም ወደ ሕዝብ አሳ​ደ​ዳ​ቸው። የጸኑ ከተ​ሞ​ች​ንም አፈ​ረሰ፤ የመ​ኳ​ን​ን​ቱ​ንም ቤት ጣለ።

15 ቀባ​ጣሪ አን​ደ​በት ደጋግ ሴቶ​ችን ከባ​ሎ​ቻ​ቸው ቤት አስ​ወ​ጥታ ሰደ​ደ​ቻ​ቸው፤ ገን​ዘ​ባ​ቸ​ው​ንም አጠ​ፋ​ች​ባ​ቸው።

16 ከእ​ር​ስዋ ያል​ተ​ጠ​በቀ ሰው ግን ለዘ​ለ​ዓ​ለሙ አያ​ር​ፍም፤ በሰ​ላ​ምም አይ​ኖ​ርም።

17 የግ​ር​ፋት ቍስል መግል ይይ​ዛል፤ የአ​ን​ደ​በት ቍስል ግን አጥ​ን​ትን ይሰ​ብ​ራል።

18 በጦር የወ​ደቁ ሰዎች ብዙ ናቸው፤ ነገር ግን በአ​ን​ደ​በት እንደ ጠፉ አይ​ደ​ሉም።

19 ከእ​ርሷ የዳ​ነና በጥ​ፋ​ትዋ ያል​ተ​ሰ​ነ​ካ​ከለ፥ በቀ​ን​በ​ሯም ያላ​ረሰ፥ በእ​ግር ብረ​ት​ዋም ያል​ታ​ሰረ ብፁዕ ነው።

20 ቀን​በ​ርዋ የብ​ረት ቀን​በር ነውና፤ እግር ብረ​ቷም የብ​ርት ነውና።

21 ሞት​ዋም ክፉ ሞት ነው፤ ከእ​ር​ስ​ዋም ሲኦል ትቀ​ላ​ለች።

22 በጻ​ድ​ቃን ግን አት​ደ​ር​ስ​ባ​ቸ​ውም፤ በእ​ሳ​ቷም አይ​ቃ​ጠ​ሉም።

23 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የዘ​ነጉ ሰዎች በእ​ር​ስዋ ይወ​ድ​ቃሉ፤ በማ​ይ​ጠፋ እሳ​ት​ዋም ታቃ​ጥ​ላ​ቸ​ዋ​ለች። እንደ አን​በ​ሳም ትወ​ረ​ወ​ር​ባ​ቸ​ዋ​ለች፤ እንደ ነብ​ርም ትይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለች።

24 ንብ​ረ​ት​ህን በእ​ሾህ ብታ​ጥር፥ ወር​ቅ​ህ​ንና ብር​ህ​ንም ብት​ቈ​ልፍ፥

25 ነገ​ር​ህን በሚ​ዛን ብት​መ​ዝን፥ ለአ​ፍ​ህም መዝ​ጊ​ያና ቍልፍ ብታ​ደ​ርግ፥

26 ዳግ​መ​ኛም በአ​ን​ደ​በ​ትህ እን​ዳ​ት​ሰ​ነ​ካ​ከል፥ በሚ​ያ​ድ​ን​ህም ፊት እን​ዳ​ት​ጥ​ልህ ተጠ​በቅ።