የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽሐፈ ሲራክ 10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽሐፈ ሲራክ 10

1 ጠቢብ ንጉሥ ሕዝ​ቡን ይመ​ክ​ራል፥ አስ​ተ​ዋይ ዳኛም ሥር​ዐ​ትን ይሠ​ራል።

2 ሎሌ​ውም እንደ ሕዝቡ አለቃ ነው፤ የከ​ተ​ማው ገዥ እን​ደ​ሚ​ሠ​ራው በው​ስጧ የሚ​ኖሩ ሰዎች ይሠ​ራሉ።

3 አላ​ዋቂ ንጉሥ ሕዝ​ቡን ያጠ​ፋል፤ ሀገ​ርም በሽ​ማ​ግ​ሌ​ዎች ጥበብ ትጸ​ና​ለች።

4 የም​ድር ግዛት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ነው፥ በጊ​ዜ​ውም የሚ​ጠ​ቅ​መ​ውን ሰው በእ​ር​ስዋ ላይ ያስ​ነ​ሣል።

5 የሰው በረ​ከቱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ ነው፥ በጸ​ሓ​ፊም ሰው​ነት ክብ​ሩን ያኖ​ራል።

በት​ዕ​ቢት የሚ​መጣ ኀጢ​አት

6 ባል​ን​ጀ​ራ​ህን በሳ​ተ​በት ሁሉ አት​ን​ቀ​ፈው፥ በነ​ቀ​ፋ​ህም ምንም ክፉ ነገር የም​ታ​ደ​ር​ግ​በት አይ​ኑር።

7 ትዕ​ቢት በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና በሰው ዘንድ የተ​ጠላ ነው፥ ከሁ​ሉም ዐመፅ ትከ​ፋ​ለች።

8 መን​ግ​ሥ​ትም ስለ ዐመ​ፅና ክር​ክር፥ ስለ ገን​ዘ​ብም፥ ካንዱ ወገን ወደ ሌላው ወገን ትፈ​ል​ሳ​ለች።

9 እን​ግ​ዲህ ትቢ​ያና ዐመድ የሚ​ሆን፥ በሕ​ይ​ወ​ትም ሳለ ሰው​ነቱ የሚ​ተላ ሰው ለምን ይታ​በ​ያል?

10 የሰፋ ቍስ​ልን ባለ መድ​ኀ​ኒት ያድ​ነ​ዋል፤ ንጉሥ መባል ግን ለዛሬ ብቻ ነው፥ ነገም ይሞ​ታል።

11 ሰውም ከሞተ በኋላ የትል ዕድል ፋንታ ይሆ​ናል።

12 የት​ዕ​ቢት መጀ​መ​ሪያ ሰውን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትለ​የ​ዋ​ለች፤ ልቡ​ና​ው​ንም ከፈ​ጣ​ሪው ታር​ቀ​ዋ​ለች።

13 ትዕ​ቢት የኀ​ጢ​አት መጀ​መ​ሪያ ናት፤ በአ​ጸ​ና​ትም ሰው ላይ ርኵ​ሰ​ትን ታበ​ዛ​በ​ታ​ለች፥ ስለ​ዚ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የት​ዕ​ቢ​ተ​ኞ​ችን ፍዳ ይገ​ል​ጣል፥ ፈጽ​ሞም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ቆ​ችን ዙፋን ያፈ​ር​ሳል፤ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ የዋ​ሃ​ንን ይሾ​ማል።

15 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ሥራ​ቸ​ውን ነቀለ፥ በእ​ነ​ር​ሱም ፋንታ ትሑ​ታ​ንን ተከለ።

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የአ​ሕ​ዛ​ብን ሀገ​ሮች አጠፋ፥ እስከ ምድር መሠ​ረት ድረስ አጠ​ፋ​ቸው።

17 ፈጽ​ሞም አጠ​ፋ​ቸው፥ ስም አጠ​ራ​ራ​ቸ​ው​ንም ከም​ድር ደመ​ሰሰ።

18 ትዕ​ቢት ለሰው የተ​ፈ​ጠረ አይ​ደ​ለም፥ ቍጣና ጥፋ​ትም ከሴት ለሚ​ወ​ለድ ሰው አይ​ደ​ለም።

ክብር ስለ​ሚ​ገ​ባ​ቸ​ውና ስለ​ማ​ይ​ገ​ባ​ቸው

19 የሰው ዘር የከ​በረ ዘር ነው፥ የከ​በረ ዘር ማን​ነው? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሰዎች ዘር አይ​ደ​ለ​ምን?

20 የሰው ዘር የጐ​ሰ​ቈለ ዘር ነው፥ ጐስ​ቋ​ላው ዘር ማን​ነው? የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትእ​ዛዝ የማ​ይ​ጠ​ብቁ ሰዎች ዘር አይ​ደ​ለ​ምን?

21 ዳኛ ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ይልቅ የከ​በረ ነው፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈሩ ሰዎች ግን ከእ​ርሱ ይልቅ ይከ​ብ​ራሉ።

22 ለባ​ለ​ጸ​ጋ​ውና ለከ​በ​ር​ቴው ለድ​ሃ​ውም ክብ​ራ​ቸው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መፍ​ራት ነው።

23 ድሃ​ውን ስለ ድህ​ነቱ ይን​ቁት ዘንድ አይ​ገ​ባም፥ ኀጢ​አ​ተ​ኛ​ው​ንም ሰው ስለ ባለ​ጸ​ግ​ነቱ ያከ​ብ​ሩት ዘንድ አይ​ገ​ባም።

24 ታላ​ላ​ቆ​ችና አለ​ቆች፥ መኳ​ን​ን​ቱም ይከ​ብ​ራሉ፤ ከእ​ነ​ር​ሱም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ፈራ ሰውን የሚ​በ​ል​ጠው የለም።

25 ጠቢብ ቤተ ሰብ በን​ጹሕ ያገ​ለ​ግ​ላል፥ ዐዋቂ ሰውም አይ​ነ​ቅ​ፈ​ውም።

26 ሥራ​ህን ስት​ሠራ አት​ራ​ቀቅ፥ በች​ግ​ር​ህም ወራት አት​መካ።

27 ከሚ​ዞ​ርና ከሚ​መካ፥ ምግ​ቡ​ንም ከማ​ያ​ገኝ ሰው ይልቅ፥ የሚ​ያ​ር​ስና የሚ​ቈ​ፍር ይሻ​ላል።

28 ልጄ ሆይ፥ በየ​ዋ​ህ​ነ​ትህ ሰው​ነ​ት​ህን ደስ አሰ​ኛት፥ የተ​ቻ​ለ​ህ​ንም ያህል አዘ​ጋ​ጃት።

29 ለራሱ የሚ​ነ​ፍግ ለማን ቸር ይሆ​ናል? ሰው​ነ​ቱን የማ​ያ​ዘ​ጋ​ጃ​ትን ሰውስ ማን ያመ​ሰ​ግ​ነ​ዋል?

30 ድሃ​ውን ስለ ጥበቡ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል፥ ባለ​ጠ​ጋ​ውን ግን ስለ ባለ​ጠ​ግ​ነቱ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።

31 በተ​ቸ​ገረ ጊዜ የማ​ያ​ዝን ሰው፥ በተ​ዘ​ጋጀ ጊዜ እን​ዴት ደስ ይለው?