የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች

መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን


መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ካልእ 12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)
መጽ​ሐፈ መቃ​ብ​ያን ካልእ 12

1 በድ​ን​ኳኑ ውስጥ ያዘ​ዛ​ች​ሁን ያል​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ ከራ​ሳ​ች​ሁም ፈቃድ በቀር ፈቃ​ዱን ያላ​ደ​ረ​ጋ​ችሁ የእ​ስ​ራ​ኤል ኀያ​ላን ወዮ​ላ​ችሁ! ይኸ​ውም ትዕ​ቢ​ትና ትዝ​ኅ​ርት፥ ዝሙ​ትና ስስት፥ ስካ​ርና መጠጥ፥ በሐ​ሰ​ትም መማል ነው።

2 ስለ​ዚ​ህም ቍጣዬ በእ​ሳት ፊት እንደ አለ ገለባ በእ​ና​ንተ ላይ ይነ​ድ​ዳል፤ ተራ​ራ​ው​ንም እን​ደ​ሚ​ያ​ቃ​ጥል እሳት፥ የደ​ቀ​ቀ​ው​ንም ትቢያ ከም​ድር አፍሶ ከሥ​ራው የተ​ነሣ ፍለ​ጋው ወደ​ማ​ይ​ገ​ኝ​በት ወደ ሰማይ እን​ደ​ሚ​በ​ት​ነው፥ እንደ ዐውሎ ነፋስ፥

3 እን​ዲሁ ክፋ​ትን የሚ​ሠ​ሩ​አ​ትን ሁሉ አጠ​ፋ​ቸ​ዋ​ለሁ ይላል የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር። ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አስ​ቡት፤ የሚ​ሳ​ነ​ውም የለም።

4 የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል፤ በት​እ​ዛ​ዙም የሚ​ሄ​ዱ​ትን በደ​ላ​ቸ​ው​ንና ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ቸ​ዋል፤ በአ​ለ​ማ​መ​ንም ደን​ቆ​ሮ​ዎ​ችና የልብ ፈዛ​ዞች አት​ሁኑ።

5 ልቡ​ና​ች​ሁ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀና አድ​ርጉ፤ ነፍ​ሳ​ች​ሁን ታድኑ ዘንድ በእ​ርሱ እመኑ፤ በመ​ከ​ራ​ች​ሁም ቀን ከጠ​ላ​ታ​ችሁ እጅ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ።

6 በም​ት​ጠ​ሩ​ኝም ጊዜ እነሆ ከእ​ና​ንተ ጋር አለሁ እላ​ች​ኋ​ለሁ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁም እጅ አድ​ና​ች​ኋ​ለሁ፤ በእ​ኔም አም​ና​ች​ኋ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አድ​ር​ጋ​ች​ኋ​ልና፥ ከሕ​ጌም አል​ወ​ጣ​ች​ሁ​ምና፥ እኔ የም​ወ​ደ​ውን ወዳ​ች​ኋ​ልና በመ​ከ​ራ​ችሁ ቀን ቸል አል​ላ​ች​ሁም ይላል ሁሉን የሚ​ገዛ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

7 የሚ​ወ​ድ​ዱ​ት​ንም ይወ​ድ​ዳ​ቸ​ዋል፤ ርኅ​ሩ​ህና ይቅር ባይ ነውና፥ ትእ​ዛ​ዙን የሚ​ጠ​ብ​ቁ​ትን ይጠ​ብ​ቃ​ቸ​ዋል።

8 ቍጣ​ው​ንም ብዙ ጊዜ ይመ​ል​ስ​ላ​ቸ​ዋል፤ ሥጋ​ዊና ደማዊ እንደ ሆኑ የሚ​ያ​ው​ቃ​ቸው ስለ ሆነ ይቅር ባይ ነውና፥ በመ​ቅ​ሠ​ፍቱ ሁሉ አያ​ጠ​ፋም፤ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም ከሥ​ጋ​ቸው በተ​ለ​የች ጊዜ ወደ መሬ​ት​ነ​ታ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ።

9 ካለ​መ​ኖር ፈጥ​ሯ​ቸ​ዋ​ልና፥ ካለ​መ​ኖር ያመ​ጣ​ቸው ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እስ​ኪ​ወድ ድረስ የሚ​ኖ​ሩ​በ​ትን ቦታ አያ​ው​ቁም፤ ዳግ​መ​ኛም እርሱ ነፍ​ሳ​ቸ​ውን ወሰደ፤ የመ​ሬት ባሕ​ር​ይ​ንም ወደ መሬ​ት​ነቱ መለሰ።

10 ዳግ​መ​ኛም ፈቃዱ ካለ​መ​ኖር ወደ መኖር ያመ​ጣ​ቸ​ዋል።

11 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የካደ ጺሩ​ጻ​ይ​ዳን ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መታ​በ​ይን አበዛ፤ እስከ ወደ​ደ​ባ​ትም ቀን ድረስ በተ​ወው ጊዜ ራሱን ከፍ ከፍ አደ​ረገ።

12 እን​ዲ​ህም አለ፥ “ዘመኔ እንደ ሰማይ ዘመን ሆነ፤ ፀሐ​ይ​ንም የማ​ወጣ እኔ ነኝ፤ እስከ ዘለ​ዓ​ለ​ምም ድረስ አል​ሞ​ትም።”

13 ይህ​ንም ነገር ተና​ግሮ ሳይ​ጨ​ርስ ስሙ ጥል​ም​ያ​ኮስ የሚ​ባል መል​አከ ሞት ወርዶ ልቡን መታው፤ በዚ​ያ​ችም ሰዓት ሞተ፤ ፈጣ​ሪ​ውን አላ​መ​ሰ​ገ​ነ​ው​ምና ከት​ዕ​ቢቱ ብዛት፥ ከሥ​ራ​ውም ክፋት የተ​ነሣ ከአ​ማረ ኑሮው ተለ​ይቶ ጠፋ።

14 የከ​ለ​ዳ​ው​ያን ንጉሥ ሠራ​ዊት ግን ሊወ​ጉት ወድ​ደው፥ ከከ​ተ​ማ​ውና ከአ​ገሩ አደ​ባ​ባይ ውጭ ሰፍ​ረው ሳሉ በሞተ ጊዜ ወጥ​ተው ሀገ​ሩን አጠፉ፤ ከብ​ቱ​ንም ሁሉ ዘረፉ፤ ከቅ​ጥር እስ​ከ​ሚ​ጠጋ ወንድ ድረስ አላ​ስ​ቀ​ሩም።

15 ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ዘረፉ፤ ቈሳ​ቍ​ሱ​ንም ወሰዱ፤ ከተ​ማ​ው​ንም በእ​ሳት አቃ​ጥ​ለው ወደ ሀገ​ራ​ቸው ተመ​ለሱ።