መዝሙር 133 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መዝሙር 1331 የዳዊት የዕርገት መዝሙር።1 የዳዊት የዕርገት መዝሙር። ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ እንዴት መልካም፥ እንዴት ውብ ነው። 2 ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም እንደሚፈስስ፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው። 3 በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፥ በዚያ ጌታ በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘለዓለም አዝዞአልና። |